የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የአምስት አመት ስትራቴጂክ ዕቅድ (2008 – 2012)
ኢትዮጵያ በ2017 የመጀመሪያ ደረጃ የመካከለኛ ገቢ ያላቸው ሀገራት ተርታ ለመሰለፍ እያደረገች ያለችውን ጥረት ዕውን ለማድረግ ይረዳ ዘንድ አንደኛው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በሁሉም ሴክተር ተነድፎ ላለፉት አምስት አመታት ሲተገበር ቆይቷል፡፡ በዚህም በርካታ ሀገርን የሚለውጡ ውጤቶች በመመዝገብ ላይ ይገኛሉ፡፡ የተገኙትን ውጤቶች እያጎለበቱ በቀጣይነት ወደፊት ለመጓዝ እንዲቻል በሁለተኛው የዕድገትና ትራንሰፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ሀገሪቷ ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ የምታደርገውን ሽግግር፣በከተማ አስተዳደር የተቀመጠዉን የ አምስት አመት ግብ ታሳቢ በማድረግ ይህንን እቅድ ማዘጋጀት እና ወደ ትግበራ መግባት አስፈልጓል፡፡