የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ለስድስተኛ ዙር የሰጠው የጀማሪ አመራር ስልጠና ከተቀመጠለት ግብ አንፃር በስኬት መጠናቀቁን የስልጠናውን አፈፃፀም አስመልክቶ የፌዴራል እና ክልል አካዳሚዎች ተካፋይ በሆኑበት መድረክ ግምገማ ላይ ተገለፀ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም ቀጣይ የሚሰጡ ስልጠናዎች ከዚህ በፊት የታዩ ክፍቶችን በማረም የተሻለ የአሰለጣጠን አካሄድን በመከተል ሰልጣኞችን መቅረጽ እንደሚገባ አቀጣጫ ተቀምጧል፡፡ የስልጠናውን ሂደት ተመርኩዞ የተሰራው የዳሰሳ ጥናት በመድረኩ ላይ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ጥናቱ መቅረቡም የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎችን አጉልቶ ለማየት እንደሚያስችል ተጠቅሷል፡፡

Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published.