የኢንስቲትዩቱን የአፈጻጸም ችግሮች ለመፍታት የተቋሙ ሰራተኞች በጋራ መረባረብ እንዳለባቸው ተገለጸ

new1
የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ የስራ አመራር ኢንስቲትዩት የ2012 በጀት ዓመት የስድስት ወር ዕቅድ አፈፃፀምን ካለበት ዝቅተኛ ደረጃ በማላቀቅ በቀሪ ወራት የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንዲቻል የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች በጋራ መረባረብ እንዳለባቸው የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀርጋሞ ሀማሞ ገለጹ፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ እንደተናገሩት ኢንስቲትዩቱ በአዲስ መልክ ከተዋቀረ በኋላ በአዋጅ በተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መሰረት የበጀት ዓመቱን ተግባራት በማቀድ ወደ ስራ የገባ ቢሆንም በታሰበው ልክ አጥጋቢ የሚባል ውጤት ማስመዝገብ አልቻለም፡፡ እንዲሁም በዚህ ግማሽ ዓመት ከስራ ሠዓት አጠቃቀም ጀምሮ በግል ስራ የመጠመድና መሰል ጉድለቶች ታይተዋል፡፡ የሞርኒንግ ብሪፊንግ ውይይቶች ያመጡትን ለውጥ እየገመገሙ መሄድ ባለመቻሉም አፈፃፀማችን ደካማ እንዲሆን አድርጎታል ብለዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም የዕቅድና የሪፖርት ዝግጅት ጥራት መጓደል እንዲሁም ስራን በራስ ተነሳሽነት አለማከናወን ለአፈጻጸሙ ማነስ ተጨማሪ ምክንያቶች መሆናቸውን ጠቅሰው ሁሉም አመራርና ሰራተኛ ድክመቶችን ለማረም እና በቀሪ ወራት የተሸለ ውጤት ለማስመዝገብ በጋራ መረባረብ ይጠበቅበታል ሲሉ በአፅንኦት ገልጸዋል፡፡
new2

ኢንስቲትዩቱ በጥናት በለያቸው ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ስልጠና መስጠት መጀመሩን አስታወቀ

ዜና
ኢንስቲትዩቱ በጥናት በለያቸው ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ስልጠና መስጠት መጀመሩን አስታወቀ
የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ የስራ አመራር ኢንስቲትዩት በከተማ አስተዳደደሩ ከሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች ናሙና በመውሰድ ባደረገው የስልጠና ፍላጎት ጥናት 18 የሚሆኑ የስልጠና ርዕሰ ጉዳዮች ተለይተዋል፡፡ ይህን መነሻ በማድረግም ከየካቲት 24/2/2012 ዓ.ም ጀምሮ ስልጠና መስጠት መጀመራቸውን በኢንስቲትዩቱ የስልጠና ፕሮጋራሞች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዘለቀ ሳሙኤል አስታውቀዋል፡፡
እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ ርዕሰ ጉዳዮች ከተለዩ በኋላ የትኛው ስልጠና ቅድሚያ ይሰጥ የሚለውን ለመለየት በተደረገው የፍላጎት ጥናት መሰረት አብዛኞቹ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የጊዜ አጠቃቀምና የመልካም አስተዳደር ችግሮች የሚሉትን በመምረጣቸው ምክንያት 165 የሚሆኑ ባለሙያዎች የመጀመሪያውን ዙር ስልጠና እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡ ከስልጠናው በፊት እና በኋላ ፈተና በመስጠት በስልጠናው ያመጡት ለውጥ እንደሚገመገምም ተናግረዋል፡፡
እንደ ከተማ አስተዳደደርም ሆነ እንደ ሀገር ተግባርን ተረድቶ በጊዜውና በወቅቱ እንዲሁም በቅልጥፍና ተገልጋይን ከማርካት ብሎም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከመፍታት አኳያ ሰፊ ክፍተት ይታያል፡፡ ይህን ችግር ለመቅረፍና የተጀመረውን ለውጥ በአስተማማኝ መልኩ ለማስቀጠል ስልጠናው አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን አቶ ዘለቀ አብራርተዋል፡፡ ስልጠናውን እየወሰዱ የሚገኙ ባለሙያዎች ከስልጠናው በኋላ ያላቸውን የግንዛቤ ደረጃ በማሳደግ በአገልጎሎት አሰጣጥ፣ በጊዜ አጠቃቀምና በመልካም አስተዳደር ላይ የሚታዩ ችግሮችን በራሳቸው አቅም በመፍታት ውጤታማ ስራ ይሰራሉ ተብሎ ስለሚጠበቅ ባለሙያዎች ስልጠናውን በትኩረት እንዲከታተሉ ዳይሬክተሩ አሳስበዋል፡፡
በመጨረሻም እስከ በጀት ዓመቱ ማጠናቀቂያ ድረስ በተለዩት የስልጠና ርዕሶች ዙሪያ ከ4 ሺህ 500 በላይ ሰልጣኞች ስልጠናውን እንደሚወሰዱ የኢንስቲትዩቱ የህዝብ ግንኙነት ቡድን ዘገባ ያመለክታል፡፡
4IMG_0635

IMG_0653

IMG_0658IMG_0644IMG_0653IMG_0658