ተቋማዊ ለውጡን ከሀገራዊና ከከተማዋ ለውጥ ጋር አስተሳስሮ መምራት እንደሚገባ ተጠቆመ

dddd4dd3dd1የአዲስ አበባ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት የ2012 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ10 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ነሀሴ 8
እና 9 2012 ዓመተ ምህረት በነጋ ቦንገር ሆቴል በገመገመበት ወቅት ተቋማዊ ለወጡን ከሀገራዊና ከከተማዋ ለውጥ ጋር
አስተሳስሮ መምራት እንደሚገባ ሪፖርቱን ያቀረቡት የዕቅድና በጀት ዝግጅት ክትትል ዳይሬክቶሬት ተወካይ ዳይሬክተር አቶ ዘላለም
ክበበው ገልፀዋል፡፡
የስልጠና ምርምር አገልግሎቶቻን የፍላጎት ዳሰሳ ጥናትን መሰረት ያደረጉ መሆኑ፣ በኮቪድ-19 ሳይበገሩ መረጃዎችን በማሰባሰብና
የትርፍ ጊዜን ሁሉ ተጠቅሞ በቴክኖሎጂ ታግዞ የጥናትና ምርምር ስራዎች እንዲጠናቀቁ መደረጋቸው በአወንታ የሚጠቀሱ
ተጋብራት እንደነበሩ አክለው ተናግረዋል፡፡
ሀገራዊ ለውጡ በሚፈለገው አስተሳሰብ አቅምና ቁመና ላይ ሆነን አገልግሎት መስጠት አለመቻላችን በዚህም የተነሳ የስልጠና
ሞጁሎች በይዘትም ይሁን በአዘገጃጀት በለውጡ የተቃኙ እንዳይሆኑ ተብሎ በክፍተት ተገምግሟል ፡፡

የኢንስቲትዩቱ የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ደርቤ ፈለቀ የኮቪድ-19 ስራዎችን አስመልክተው ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን ወረርሽኙ
በሀገራችን ከተከሰተ በኋላ በፍጥነት ግብረሀይል በማቋቋም ወደ ስራ መገባቱን ተናግረዋል፡፡ ተቋሙ ከመንግስትና ከጤና ተቋማት
የሚወርዱ መመሪያዎችን በመቀበል ለመተግበር ጥረት አድርጓል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ስራ አመራር ኢስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተርና የጥናትና ምርምር ማማከር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ምንደፍሮ ሀይሌ ለውጡን
አስመልክተው ባቀረቡት ሰነድ እና ማጠቃለያ ላይ እንደተናገሩት የተሟላ አገልግሎት መስጠት ከተፈለገ ለውጡን በቁርጠኝነት
ማረጋገጥ ግዴታ ነው፡፡ እናም በዕቅዳችን መሰረት የተሟላ አገልግሎት በመስጠት ተገልጋዩን ማርካትና የተቋሙን ተልዕኮ ማሳካት
ለነገ የማይባል ተግባር በመሆኑ ሁሉም ኃላፊው በአፅንኦት አስገንዝበዋል፡፡
መረጃው የአዲስ አበባ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት የህዝብ ግንኙነት ቡድን ነው፡፡

የኢንስቲትዩቱን የአፈጻጸም ችግሮች ለመፍታት የተቋሙ ሰራተኞች በጋራ መረባረብ እንዳለባቸው ተገለጸ

new1
የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ የስራ አመራር ኢንስቲትዩት የ2012 በጀት ዓመት የስድስት ወር ዕቅድ አፈፃፀምን ካለበት ዝቅተኛ ደረጃ በማላቀቅ በቀሪ ወራት የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንዲቻል የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች በጋራ መረባረብ እንዳለባቸው የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀርጋሞ ሀማሞ ገለጹ፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ እንደተናገሩት ኢንስቲትዩቱ በአዲስ መልክ ከተዋቀረ በኋላ በአዋጅ በተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መሰረት የበጀት ዓመቱን ተግባራት በማቀድ ወደ ስራ የገባ ቢሆንም በታሰበው ልክ አጥጋቢ የሚባል ውጤት ማስመዝገብ አልቻለም፡፡ እንዲሁም በዚህ ግማሽ ዓመት ከስራ ሠዓት አጠቃቀም ጀምሮ በግል ስራ የመጠመድና መሰል ጉድለቶች ታይተዋል፡፡ የሞርኒንግ ብሪፊንግ ውይይቶች ያመጡትን ለውጥ እየገመገሙ መሄድ ባለመቻሉም አፈፃፀማችን ደካማ እንዲሆን አድርጎታል ብለዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም የዕቅድና የሪፖርት ዝግጅት ጥራት መጓደል እንዲሁም ስራን በራስ ተነሳሽነት አለማከናወን ለአፈጻጸሙ ማነስ ተጨማሪ ምክንያቶች መሆናቸውን ጠቅሰው ሁሉም አመራርና ሰራተኛ ድክመቶችን ለማረም እና በቀሪ ወራት የተሸለ ውጤት ለማስመዝገብ በጋራ መረባረብ ይጠበቅበታል ሲሉ በአፅንኦት ገልጸዋል፡፡
new2

ኢንስቲትዩቱ በጥናት በለያቸው ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ስልጠና መስጠት መጀመሩን አስታወቀ

ዜና
ኢንስቲትዩቱ በጥናት በለያቸው ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ስልጠና መስጠት መጀመሩን አስታወቀ
የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ የስራ አመራር ኢንስቲትዩት በከተማ አስተዳደደሩ ከሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች ናሙና በመውሰድ ባደረገው የስልጠና ፍላጎት ጥናት 18 የሚሆኑ የስልጠና ርዕሰ ጉዳዮች ተለይተዋል፡፡ ይህን መነሻ በማድረግም ከየካቲት 24/2/2012 ዓ.ም ጀምሮ ስልጠና መስጠት መጀመራቸውን በኢንስቲትዩቱ የስልጠና ፕሮጋራሞች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዘለቀ ሳሙኤል አስታውቀዋል፡፡
እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ ርዕሰ ጉዳዮች ከተለዩ በኋላ የትኛው ስልጠና ቅድሚያ ይሰጥ የሚለውን ለመለየት በተደረገው የፍላጎት ጥናት መሰረት አብዛኞቹ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የጊዜ አጠቃቀምና የመልካም አስተዳደር ችግሮች የሚሉትን በመምረጣቸው ምክንያት 165 የሚሆኑ ባለሙያዎች የመጀመሪያውን ዙር ስልጠና እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡ ከስልጠናው በፊት እና በኋላ ፈተና በመስጠት በስልጠናው ያመጡት ለውጥ እንደሚገመገምም ተናግረዋል፡፡
እንደ ከተማ አስተዳደደርም ሆነ እንደ ሀገር ተግባርን ተረድቶ በጊዜውና በወቅቱ እንዲሁም በቅልጥፍና ተገልጋይን ከማርካት ብሎም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከመፍታት አኳያ ሰፊ ክፍተት ይታያል፡፡ ይህን ችግር ለመቅረፍና የተጀመረውን ለውጥ በአስተማማኝ መልኩ ለማስቀጠል ስልጠናው አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን አቶ ዘለቀ አብራርተዋል፡፡ ስልጠናውን እየወሰዱ የሚገኙ ባለሙያዎች ከስልጠናው በኋላ ያላቸውን የግንዛቤ ደረጃ በማሳደግ በአገልጎሎት አሰጣጥ፣ በጊዜ አጠቃቀምና በመልካም አስተዳደር ላይ የሚታዩ ችግሮችን በራሳቸው አቅም በመፍታት ውጤታማ ስራ ይሰራሉ ተብሎ ስለሚጠበቅ ባለሙያዎች ስልጠናውን በትኩረት እንዲከታተሉ ዳይሬክተሩ አሳስበዋል፡፡
በመጨረሻም እስከ በጀት ዓመቱ ማጠናቀቂያ ድረስ በተለዩት የስልጠና ርዕሶች ዙሪያ ከ4 ሺህ 500 በላይ ሰልጣኞች ስልጠናውን እንደሚወሰዱ የኢንስቲትዩቱ የህዝብ ግንኙነት ቡድን ዘገባ ያመለክታል፡፡
4IMG_0635

IMG_0653

IMG_0658IMG_0644IMG_0653IMG_0658

የኮረና ቫይረስ ምንነትና መከላከያ መንገዶች

ቀቀ
ከታህሳስ 2012 ዓ.ም ጀምሮ በቻይና ውሀን ግዛት ሪፖርት የተደረገው የኮረና ቫይረስ መዳረሻውን እያሰፋ ለበርካታ ሰዎች ህልፈተ ህይወትና ለሀገራት ኢኮኖሚያዊ ቀወስ ምክንያት እየሆነ መጥቷል፡፡ ቫይረሱ የኖብል ወይም አዲሱ የኮረና ቫይረስ ተብሎ ሲጠራ የነበረ ሲሆን ኮረና የሚለውን ስያሜ ያገኘው በማጉያ መነጽር ሲታይ ከአለው የአክሊል / Crown / ቅርጽ ነው፡፡
በቅርቡ የዓለም የጤና ድርጅት ኖብል ኮረና ቫይረስን ኮቪድ – 19 ( COVID – 19 ) በሚል ስያሜ ሰጥቶታል፡፡
ዲ ( D ) – በሽታን / Disease / ይወክላሉ፡፡
አዲሱ የኮረና ቫይረስ የመተንፈሻ አካልን የሚያጠቃ በሽታ ነው፡፡ ዋናው መተላለፊያ መንገድ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች በሚያስሉበትና በሚያስነጥሱበት ወቅት ከትንፋሽ ጋር ከሚወጡ ፈሳሾች ጋር በሚደረግ ንክኪ ነው፡፡

የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ የስራ አመራር ኢንስቲትዩት አመራርርና ሰራተኞች አንድነት ፓርክን ጎበኙ

A የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ የስራ አመራር ኢንስቲትዩት አመራርርና ሰራተኞች አንድነት ፓርክን ጎበኙ
የተቋሙ አመራርና ሰራተኞች ሰሞኑን ፓርኩን የጎበኙ ሲሆን ከጉብኝቱ ተሳታፊዎች መካከል አንዳንዶቹ በሰጡት አስተያየት በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰሩት ስራ መገረማቸውን ገልፀዋል፡፡
በቤተ መንግስት አካባቢ በዝግታ መራመድ ቀርቶ ዞሮ ማየት የሚከለከልበት ጊዜ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው፡፡ አሁን ግን ግቢ ውስጥ ገብቶ በነፃነት መንቀሳቀስ ብቻ ሳይሆን ያንን የሚያስፈራ ድባብ አሽቀንጥሮ የጣለ እና ለአይን መስህብ የሆነ ኢትዮጵያን በትንሽ ቦታ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነገር በመመልከታችን ተደስተናል ብለዋል፡፡
በመጨረሻም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ያመሰገኑ ሲሆን ሁላችንም ልዩነቶቻችንን አጥብበን በትብብር ብንሰራ ኢትዮጵያን በትንሽ አመታት ውስጥ መቀየር እንደምንችል በአንድነት ፓርክ ተምረናል ብለዋል፡፡ BCDEFG

እንኳን ደስ አላችሁ!

sat
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ እና የከፍታችን ማሳያ የሆነችውን ETRSS-1 የተሰኘችውን ሳተላይት ወደ ህዋ ማምጠቅ በመቻሉ የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ የስራ አመራር ኢንስቲትዩት የተሰማውን ኩራት እየገለፀ ለኢንስቲትዩቱ ሰራተኞችና ለመላው የሀገራችን ህዝቦች እንኳን ደስ አላችሁ ይላል፡፡

‹‹ህገ መንግስታዊ ቃል ኪዳናችን ለዘላቂ ሠላማችን››

  • Simple Usage
    Simple Usage
  • Huge-IT Slider
    Huge-IT Slider
    The slider allows having unlimited amount of images with their titles and descriptions. The slider uses autogenerated shortcodes making it easier for the users to add it to the custom location.
79788284_1122443847930608_2031796414664671232_n

78075418_1122444271263899_1465683909319589888_n

78572940_1122443961263930_6272136154770833408_n
የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ የስራ አመራር ኢንስቲትዩት አንኳን ለ14ኛ ጊዜ ለሚከበረው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓል በሠላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡፡የዘንድሮው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓል መሪ ቃል ‹‹ህገ መንግስታዊ ቃል ኪዳናችን ለዘላቂ ሠላማችን›› የሚል ነው፡፡
በዓሉ እስካሁን በሚያምረው ልዩነታችን ውስጥ ያቆየነውን የአንድነት እና የአብሮነት ባህል የበለጠ የምናጠናክርበት አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ ጉድለቶቻችንን ደግሞ የምንሞላበት የሰላምና የፍቅር በዓል እንዲሆን በድጋሜ እንመኛለን፡፡

ሠላሣ ሁለተኛው የፀረ ኤድስ ቀን ታስቦ ዋለ

ww
ww1
ww4
ww3
የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ ስራ አመራር ኢንሰቲትዩት አመራርና ሰራተኞች በየዓመቱ ህዳር 22 ቀን ተከብሮ የሚውለውን 32ኛውን የፀረ ኤድስ ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች አስበው ውለዋል፡፡በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሀፕኮ ጽህፈት ቤት የሜኒስትርሚንግ አጋርና ጥምረት ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ወንድሙ ደንቡ ቀኑን በማስመልከት የመያያ ፅሁፍ አቅርበዋል፡፡ በሀገራችን ቀደም ባሉት ጊዜያት በተሰራው ጠንካራ ስራ በኤች አይቪ ኤድስ የሚያዘውንና የሚሞተውን የሰው ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ ተችሎ ነበር፡፡ አሁን ግን የተፈጠረውን መዘናጋት ተከትሎ የቫየረሱ ስርጭት በፍጥነት አድማሱን እያሰፋ መምጣቱን በፅሁፋቸው አመላክተዋል፡፡ የስርጭት ምጣኔውን ለአብነት ብንመለከት በአገራችን 0.9 በመቶ በመዲናችን አዲስ አበባ ደግሞ 3.4 በመቶ እንደደረሰ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ በተለይ በአዲስ አበባ ያለው ስርጭት ወደ ወረርሽኝ ደረጃ መሸጋገሩን አቶ ወንድሙ አብራርተዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀርጋሞ ሀማሞ በበኩላቸው የአገራችን ዕድገት እውን የሚሆነው አምራችና ጤናማ ዜጋ ሲኖር ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን በዚህ በሽታ ምክንያት ይህን አምራች የሆነውን የህብረተሰብ ክፍል እያጣን እንገኛለን ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ በየትኛውም አጋጣሚ ስለበሽታው ግንዛቤ በመፍጠር ስርጭቱን መከላከልና ህይወትን መታደግ ለአፍታም ቢሆን መዘንጋት እንደሌለበት አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች በበሽታው ወላጆቻቸውን ላጡ 5 ችግረኛ ልጆች ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡
የዘንድሮው የፀረ ኤድስ ቀን ‹‹ማህበረሰብ የለውጥ አቅም ነው›› በሚል መሪ ቃል ታስቦ ውሏል፡፡