የፐብሊክ ሰርቪሱን የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ለመገንባት ጥራት ያላቸው የማሰልጠኛ ሰነዶች / modules / ወሳኝ ድርሻ እንዳላቸው ተገለጸ

ሐምሌ 08/2013 ዓ.ም
የፐብሊክ ሰርቪሱን የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ለመገንባት ጥራት ያላቸው የማሰልጠኛ ሰነዶች / modules / ወሳኝ ድርሻ እንዳላቸው ተገለጸ፡፡
የአዲስ አበባ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ከሐምሌ 07/2013 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲያካሂደው በነበረው የተከለሱ የማሰልጠኛ ሰነድ ግምገማ መድረክ ማጠቃለያ ላይ በከተሞች የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማዘመን ለአመራሩና ለባለሙያው ለሚሰጡ የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ግንባታ ስልጠናዎች በከተሞች አገልግሎት ፍላጎት እና በሰልጣኞች የትምህርት ዝግጅት ደረጃ ተቃኝታው የተዘጋጁ የማሰልጠኛ ሰነዶች ወሳኝ ድርሻ አላቸው ሲሉ በመድረኩ ላይ የተገኙ ምሁራኖችና አመራሮች ገልጸዋል፡፡
የማሰልጠኛ ሰነዶቹ ከንድፈ ሃሳብ በተጨማሪ ሰልጣኙ እውቀቱን፣ ክህሎቱን፣ አመለካከቱን እና ሙያዊ ስነ-ምግባሩን ማሳደግ የሚያስችሉ እንዲሆኑ ከተጨባጭ ገጠመኞች የሚመነጩ የመወያያ ጥያቄዎች/ cases / ሊካተቱባቸው ይገባል የሚሉ አስተያየቶች ተሰጥተዋል፡፡
በተጨማሪም ስልጠናውን ወጥና ውጤታማ ለማድረግ የአሰልጣኙ መምሪያ / trainer guideline / መዘጋጀት እንዳለበት እና ስልጠናውን የሚሰጡ አሰልጣኞች በዘርፉ ጥልቅ እውቀት ያላቸው እንዲሆኑ ማድረግ ከኢንስቲትዩቱ ይጠበቃል ተብሏል፡፡
የግምገማ መድረኩ ስድስቱንም የማሰልጠኛ ሰነዶች ይበልጥ ሊያዳብሩ የሚችሉ ሙያዊ

Posted in Uncategorized.