የኢንስቲትዩቱን የአፈጻጸም ችግሮች ለመፍታት የተቋሙ ሰራተኞች በጋራ መረባረብ እንዳለባቸው ተገለጸ

new1
የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ የስራ አመራር ኢንስቲትዩት የ2012 በጀት ዓመት የስድስት ወር ዕቅድ አፈፃፀምን ካለበት ዝቅተኛ ደረጃ በማላቀቅ በቀሪ ወራት የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንዲቻል የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች በጋራ መረባረብ እንዳለባቸው የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀርጋሞ ሀማሞ ገለጹ፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ እንደተናገሩት ኢንስቲትዩቱ በአዲስ መልክ ከተዋቀረ በኋላ በአዋጅ በተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መሰረት የበጀት ዓመቱን ተግባራት በማቀድ ወደ ስራ የገባ ቢሆንም በታሰበው ልክ አጥጋቢ የሚባል ውጤት ማስመዝገብ አልቻለም፡፡ እንዲሁም በዚህ ግማሽ ዓመት ከስራ ሠዓት አጠቃቀም ጀምሮ በግል ስራ የመጠመድና መሰል ጉድለቶች ታይተዋል፡፡ የሞርኒንግ ብሪፊንግ ውይይቶች ያመጡትን ለውጥ እየገመገሙ መሄድ ባለመቻሉም አፈፃፀማችን ደካማ እንዲሆን አድርጎታል ብለዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም የዕቅድና የሪፖርት ዝግጅት ጥራት መጓደል እንዲሁም ስራን በራስ ተነሳሽነት አለማከናወን ለአፈጻጸሙ ማነስ ተጨማሪ ምክንያቶች መሆናቸውን ጠቅሰው ሁሉም አመራርና ሰራተኛ ድክመቶችን ለማረም እና በቀሪ ወራት የተሸለ ውጤት ለማስመዝገብ በጋራ መረባረብ ይጠበቅበታል ሲሉ በአፅንኦት ገልጸዋል፡፡
new2

Posted in Uncategorized.