የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የለውጥ ስራዎችን ማጠናከር ወሳኝ ነው ተባለ

ለአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ አመራርና ሰራተኞች በለውጥ ቡድንና በሞርኒንግ ብሪፊንግ ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ የለውጥ አማካሪ የሆኑት አቶ ንጉሱ ሽመልስ ስልጠናውን ሲሰጡ እንዳሉት በከተማችን የልማት የመልካም አስተዳደር እና የሪፎርም ስራዎችን ስኬታማ ለማድረግና የዕድገት ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱን በተሟላ ሁኔታ በማሳካት የመፈፀም አቅማችንን መገንባት አስፈላጊ ነው፡፡ ይህም እውን የሚሆነው መንግስት የነደፋቸውን ፖሊሲዎች እስትራቴጂዎችና የልማትና የዲሞክራሲ ዕቅዶችን በብቃትና በፅናት መፈፀም የሚችል እንደ አንድ አካል የሚሰራ ሲቪል ሰርቪስ መፍጠር ሲቻል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ስለዚህ በምናከናውናቸው የልማት፣የሪፎርምና መልካም አስተዳደር ሰራዎቻችን ዙሪያ መማማሪያና መገነባቢያ የሆነ በቡድን የመስራት መንፈስ መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን አሠልጣኙ አስረድተዋል፡፡train1
እንደ አቶ ንጉሱ ማብራሪያ የለውጥ ቡድን እና የሞርኒግ ብሪፊንግ ውይይቶችን ትኩረት ሰጥቶ ማካሄድ ከተቻለ በቀላሉ የለውጥ ሰራዊት መገንባት ይቻላል፡፡ የለውጥ ሰራዊት ከተገነባ ደግሞ በቃላሉ የመልካም አስተዳደርም ሆነ የኪራይ ሰብሳቢነት ችግሮችን መፍታት ይቻላል፡፡ ከበፊቱ አንድ ለአምስት የአሁኑ ሞርኒንግ ብሪፊኒግ የስም ለውጥ ከማድረግ የዘለለ ልዩነት የላቸውም ያሉት አሰልጣኙ በፊት ከነበረን እንቅስቃሴ በተሸለ ለመፈፀምና ለመነቃቃት ሲባል ብቻ የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡ ስለዚህ እርስ በእርስ በመገነባባት የለውጡን ጉዞ ማሳካት ከሁሉም ሰርቪስ ሰርቫንት ይጠበቃል፡፡ በስልጠናው የለውጥ ቡድን እና ሞርኒንግ ብሪፊንግ፣በእስታንዳርድ ንፅፅር የተግባር ምዝገባና ምርጥ ተሞክሮ መቀመርና ማስፋት በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ የአካዳሚው አመራርና ሠራተኞች ስልጠና ወስደዋል፡፡train2
ከሰልጣኞች መካከል አንዳንዶቹ ስልጠናው የተቋሙን ራዕይና ተልዕኮ በተሟላ መልኩ ለመፈፀም አጋዥ ከመሆኑም በላይ እየተፋዘዘ የመጣውን የአንድ ለአምስት እና የለውጥ ቡድን ውይይት የሚያነቃቃ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ምርጥ ተሞክሮዎችን እንዴት መቀመርና ማስፋት እንዳለብን ግብዓት ያገኘንበት ነው ያሉት ሠልጣኞች በቀጣይ ትኩርት ሰጥተን በመስራት ለዕቅዳች ብሎም ለተቋሙ ስኬት የድርሻችንን ለማበርከት ተዘጋጅተናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published.