የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ከፌደራል መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ጋር በመቀናጀት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከ5 ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ለተወጣጡ ለ472 የወጣቶች ሊግ አመራሮች ስልጠና መስጠቱን የአካዳሚው ም/ ዋና ዳይሬክተር እና የአካዳሚክ ጉዳዮች ዘርፍ ሃላፊ አቶ ሐርጋሞ ሐማሞ ገለፁ፡፡

ሰልጠናው በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደ ተሰጠና በአምስቱም የክልል መስተዳድር የአመራር አካዳሚዎች ከ5000 በላይ የወጣቶች ሊግ አመራሮች ስልጠናውን መከታተል እንደቻሉ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡ የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚም ከተመደቡለት 500 ሰልጣኞች ውስጥ ወንድ 367 ሴት 105. በድምሩ 472 ሰልጣኞችን ተቀብሎ ማሰልጠኑን አያይዘው ገልጸዋል፡፡

 በተጨማሪም የስልጠናው ዋና አላማ  የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ አመራሮችን የማስፈፀም አቅም በመገንባትና ተልዕኳቸውን በተገቢው በመረዳት በእውቀት ላይ የተመሰረተ አመራር መሰጠት የሚችሉበትን አቅም ማጎልበት መሆኑን አሰረድተዋል፡፡ ወጣት አመራሮቹ ከተለያዩ ክልሎች እንደ መምጣታቸው መጠን በስልጠና ቆይታቸው በየክልላቸው የሚሰሩ የልማትና የዴሞክራሲ ግንባታ ተግባራት ላይ ልምድ ሊለዋወጡ የሚችሉበት እድል እንደተፈጠረላቸው ተናግረዋል፡፡

 

Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published.