የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ባለሙያዎች እውቅና ሰጠ

cdba አካዳሚው ህዳር 22 ቀን 2010 ዓመተ ምህረት በጌትፋም ሆቴል የመጀመሪያውን ሩብ ዓመት ሪፖርት ግምገማ ባካሄደበት ወቅት በ2009 በጀት ዓመት የተሰጣቸውን ተግባር በላቀ ደረጃ በመፈጸም እና ሞዴል ሊሆኑ የሚችሉ ተግባራትን አከናውነዋል ላላቸው ሶስት ባለሙያዎች ከ1500 ብር እስከ 2500 ብር የሚደርስ የቦንድ ሽልማት አበርክቷል፡፡ በሌላ በኩል አካዳሚው ድረ-ገጽ እንዲኖረው ላደረጉ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ክፍል የዋንጫ እና ለቡድን መሪው የ2ሺህ ብር ቦንድ ሽልማት ተሰጥቷል፡፡
ሽልማቱን የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ሃላፊ አቶ ይሰሐቅ ግርማይ ሽልማቱን ሲሰጡ እንደተናገሩት በከተማችን ከ3ሺህ 500 በላይ አመራሮች ይገኛሉ፡፡ የከተማችንም ሆነ የሀገራችን ችግር የፖሊሲና የስትራቴጂ ሣይሆን የአፈጻጸም ችግር እንደሆነ አብራርተዋል፡፡ ከተማችን በተለያያ መልኩ ውስብሰብ እየሆነች መምጣቷን የጠቆሙት ሀላፊው ይህን ችግር መቅረፍ የሚችል አመራር መገንባት ወሳኝ ተግባር ነው፡፡ ብቁ አመራር ለመፍጠር ደግሞ ብቁ ባለሙያ ማዘጋጀት ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት የዕውቅና ሥነ-ስርዓት ሠራተኛን በማበረታታት ረገድ ጠቀሜታው የጐላ ቢሆንም የተወሰኑ ሠራተኞችን ብቻ ሣይሆን የስራ ክፍሎችንም ሆነ ተቋሙን መሸለም ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡ ይህ ሽልማት በቀጣይ የማነሣሣት ጥሩ መልዕክት የሚያስተላልፍ በመሆኑ ተጠናከሮ መቀጠል እንዳለበትም ቢሮ ኃላፊው አስገንዝበዋል፡፡
በመጨረሻም በኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት የተሰራው የአካዳሚው ድረ-ገጽ www.amzla.edu.et በአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር የፐብሊከ ሠርቪሰ ቢሮ ሃላፊ በአቶ ይሰሐቅ ግርማይ እና በአካዳሚው ዋና ዳይሬከተር በአቶ ከሐሰ ወልደማሪያም በይፋ ተመርቆ ስራ መጀመሩን መረዳት ተችሏል፡፡

Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published.