የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ከደቡብ መለስ አመራር አካዳሚ ጋር የልምድ ልውውጥ አካሄደ

Untitled2የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ከመጋቢት 14 እስከ መጋቢት 15 /2010 ዓመተ ምህረት ድረስ ከደበቡብ መለስ አመራር አካዳሚ ጋር የልምድ ልውውጥ አድርጓል፡፡ የልምድ ልውውጡ በአስተዳር ልማት ዘርፍ የተዘጋጀ ሲሆን ቡድኑን የመሩት የሰልጣኞችና የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ ወይኒቱ ወንድይራድ እንደተናገሩት የልምድ ልውውጡ በዋናነት የእርስ በርስ ግንኙነትን ከማጠናከር ባሻገር አካዳሚያችን የሰነቀውን ተልዕኮ በተሟላ መልኩ ለመፈፀም እንዲያስችለው ያለመ ነው ብለዋል፡፡ በልምድ ለውውጡ በአካዳሚው የታዘብነው ከላይ እስከታች ያለው ቅንጅታዊ አሰራር እንደ ተሞክሮ የሚወሰድ ነው፡፡ ቅንጅታዊ አሰራር በመኖሩም ባልተሟላ ግብአት ተቋሙ ተገልጋይን የሚያረካ ስራ መስራት እንዳስቻለው በተሰጠው አስተያየት ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ በአመራሩ እና በሰራተኛው መካከል ያለው የጠበቀ የስራ ግንኙነትና የአንድነት መንፈስ ሰራተኛው ወደ ውጭ ከማማተር ይልቅ ተግባሩን በባለቤትነትና በእኔነት ስሜት እንዲመለከት እና የተሻለ አገልግሎት መስጠት እንዳስቻላቸው መገንዘባቸውን አስረድተዋል፡፡

እንደ ዳይሬክተሯ ገለፃ ከፋሲሊቲ አኳያ የምግብ ዝግጅቱ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በተቋሙ የውስጥ አቅም መዘጋጀቱና በዚህም ምክንያት በፊት ይታዩ የነበሩ የጥራት ችግሮችን መቅረፍ መቻሉ የሚያበረታታ ተግባር ነው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ቀደም ሲል በምግብ ጥሬ ዕቃ አቅርቦት በኩል ይስተዋል የነበረውን  የኪራይ ሰብሳቢነት አባዜ በፅኑ ታግሎ በማስተካከል ደንበኛን ያረካ ስራ መስራት ችለዋል ያሉት ወይዘሮ ወይኒቱ በሌላ በኩል ስልጠና ሲኖር የሚሰራ ሳይኖር ደግሞ እንዲሁ ቁጭ የሚል ሰራተኛ እንዳይኖር በማሰብ ተቋሙ የስራ ዕድል ለመፍጠር የሚያደርገው ጥረትም የሚደነቅ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡ እኛም እነዚህን እና ሌሎች የተመለከትናቸውን ተሞክሮዎች ወደ አካዳሚያችን በማምጣት እና በማስፋት የሻለ አገልግሎት ለመስጠት ተዘጋጅተናል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ከልምድ ልውውጡ ተሳታፊዎች መካከል አንዳንዶቹ በሰጡት አስተያየት ከምንም በላይ የደቡብ መለስ አመራ አካዳሚ በተቋሙ ሰራተኞች ላይ የተሻለ አስተሳሰብና የአመለካከት አንድነት በመፍጠር በኩል የሰራው ስራ ከፍተኛ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ከላይ ከአመራሩ እስከታችኛው ሰራተኛ ያለው ድምፀት አንድ እንዲሆን ረድቶታል፡፡ ከዚህ ባሻገር የፅዳት ሰራተኞች ከስራ ከፅዳት በኋላ ስራ ፈትተው እንዳይቀመጡ በማሰብ የሰልጣኞችን ልብስ ከማጠብ ጀምሮ ቀለል ያሉ ሸቀጣሸቀጦችን እንዲያቀርቡ እና የስራ ዕድል ፈጥረው ገቢያቸውን እንዲያሳድጉ ለማስቻል የሚደረገው ሰናይ ተግባር በተሞክሮነት የሚወሰድ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡ በደቡብ መለስ አመራር አካዳሚ ያየናቸውን መልካም ልምዶች ወደ ተቋማችን በማምጣትና በመተግበር ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀታቸውን አስተያየት ሰጪዎቹ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

 

Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published.