የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ለሁለተኛ ዙር መካከለኛ አመራሮች ከነሀሴ 20/2009 ጀምሮ ለ42 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

የአካዳሚው የስልጠና አደረጃት ዘርፍ አስተባባሪ ዶክተር ገብረ ምሩፅ የስልጠናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ እንደተናገሩት ስልጠነ,ናው ከአራቱም ብሔራዊ ድርጅቶች እና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ለተወጣጡ ወንድ 398 ሴት 134 በአጠቃላይ ለ532 መካከለኛ አመራሮች ተሰጥቷል ብለዋል፡፡
እንደ ዶክተሩ ገለፃ ስልጠናው በዋናነት ማዕከል ያደረገው የአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ምንነት፣ ታሪካዊ አነሳስ፣ዕድገትና የወደፊት አቅጣጫ፣የአብዮዊ ዴሞክራሲ ድርጅት ግንባታ መሰረተ- መርሆዎች፣የኢትዮጵያ ፌደራስርዓት ባህሪያት፣የዴሞክራሲያዊ አንድነት ግንባታ ሂደት፣ ስኬትና የወደፊት አቅጣጫ፣የልማታዊና ዴሞክራሲያዊ አመራር ሳይንስና ጥበብ ለኢትዮጵያ ልማታዊ የህዝብ ግንኙነትና ለኮሙኒኬሽን ለኢትዮጵያ ህዳሴ እንዲሁም ከአንደኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ግቦችና የአፈፃፀም አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ስልጠና መሰጠቱን አብራርተዋል፡፡
የዓለማችን ሁኔታ በየጊዜው ተለዋዋጭ በሆነበት በዚህ ወቅት ይህ ስልጠና መዘጋጀቱ አመራሩ ከዓለም ተጨባጭ ሁኔታ ጋር እንዲራመድና እና እና ሀገራችን ያለችበትን ነባራዊ እውነታ ተረድቶ እንዲንቀሳቀስ ዕድል እንደሚፈጥርለት አስተባባሪው ተናግረዋል፡፡ በተለይ ሀገራችን የተጋረጠባትን የኪራይ ሰብሳቢነት፣የጠባብነት፣የትምክህት፣ የአክራሪነትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ሳይንሳዊ የአመራር ጥበብን ተላብሶ ለመፍታትና ለመከላከል የሚያስችል አቅም ይዞ በመውጣቱ የህብረተሰቡን እርካታ በፍጥነት በማረጋገጥ የህዳሴ ጉዟችንን ያፋጥናል ተብሎ እንደሚጠበቅ ያላቸውን እምነት ጨምረው አስረድተዋል፡፡
ስለሆነም ሁሉም ሰልጣኝ ወደ አካባቢው እንደተመለሰ ሳይውል ሳያድር የወሰደውን ስልጠና በመተግበር እና በጥልቅ ተሀድሶ ስምምነት የተደረሰባቸውን የህብረተሰቡን ቅሬታዎች በአፋጣኝ በመመለስ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን የበኩሉን እንዲወጣ ከአደራ ጭምር አሳስበዋል፡፡

Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published.