የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ከህዝብ ክንፍ ባለድርሻ አካላት ጋር የ2009 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ

Untitledአካዳሚው ጥቅምት 11 ቀን 2010 ዓ.ም ከባለድርሻ አካላት ጋርውይይት ባካሄደበት ወቅትየአካዳሚው የዕቅድ ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ደሣለኝ በሪፖርታቸው እንዳብራሩት አካዳሚያችን አመራሩን በልማታዊ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ የተቃኘ ትምህርትና ስልጠና፣ ጥናትና ምርምር እና የማማከር አገልግሎት በመስጠት የከተማችንን ሁለንተናዊ ህዳሴ የሚያረጋግጥ ብቁ አመራር እንዲሆን የመገንባት ተልእኮውን እየተገበረ ይገኛል፡፡ በተለይ በስልጠናው ዘርፍ በ2009 በጀት ዓመት ብቻ ለ1ሺህ 649 ወንድና ለ720 ሴት በአጠቃላይ ለ2ሺህ 369 በከተማዋ ውስጥ ለሚገኙ የትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎች፣ለወጣትና ሴት አመራሮች፣ለወረዳ አስተባባሪዎች የእውቀት፣ የክህሎትና የአመለካከት ክፍተቶችን መሰረት ያደረጉ በተለያዩ ርእሶች ላይ ስልጠና እንዲወስዱ መደረጉን በሪፖርታቸው ገልፀዋል፡፡
በሪፖርቱ አንደተብራራው በበጀት ዓመቱ ቁልፍ ተግባር የሆኑትን የለውጥ ሥራዎች ትኩረት ሰጥቶ ለመፈጸም ጥረት ተደርጓል፡፡ ስራዎች በተጠናከረ የለውጥ ሰራዊት ለመምራት አመራሩና ሰራተኛው በለውጥ ቡድንና በ1ለ5 አደረጃጀቶች በመታቀፍ የስራ አፈፃፀማቸውን ፣የኪራይ ሰብሳቢነትና መልካም አስተዳደር እና ሌሎች አጀንዳዎችን በመቅረፅ ግምገማ ሲያካሂዱ ከርመዋል፡፡ ይሁን እንጂ ከዘርፎቹ አኳያ ያሉትን የለዉጥ ቡድን እና የ1ለ5 ሳምንታዊ ዉይይት እንስቅስቃሴዎች ከዉይይት መቆራረጥ በተጨማሪ የሚካሄደዉ ዉይይት ችግር ፈቺና የበሰለ ከመሆን፣ ከዉጤታማነት አንፃር ፣ ምርጥ ፈፃሚን እየለዩ በመሄድ እና በተያዘው እቅድ መሰረት ሞዴል ፈፃሚዎች ፣የለውጥ ቡድኖች እንዲሁም የ1ለ5 አደረጃጀቶች በመለየት እውቅና ከመስጠት እና ከማበረታታት አኳያ ውስነንት ያለው በመሆኑ በቀጣይ ሁሉም አመራርና ሰራተኛ ለለዉጥ ሰራዊት ግንባታ ስራው ልዩ ትኩረት በመስጠት ስር ነቀል ለዉጥ ለማምጣት ሊሰራ ይገባል ሲሉ ዳይሬክተሩ አሳስበዋል፡፡
የአካዳሚው የሚዛናዊ ውጤት ተኮር አሰራር ስኮር ካርድ ለሁሉም ፈጻሚ ወርዶ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ በቀረበው ሪፖርት በበጀት ዓመቱ አምስት ልዩ ስልጠናዎች መሰጠታቸው፣ ረቂቅ ሌጅስሌሽን መዘጋጀቱ፣ በለውጥ ስራዎች ላይ ምዘና መካሄዱ፣ የአካዳሚው የድረገፅ ስራ መጠናቀቁና የታላቁ ህዳሴ

ግድብእና ግንቦት 20ን ምክንያት በማድረግ በትግራይክልል የሚገኙ የትግል ቦታዎችን ጉብኝት በተያዘው ፕሮገራም መሰረት መጎብኘት መቻሉ በጥንካሬ ከተጠቀሱ ጉዳዮች ውስጥ ጥቂቶች ናቸው፡፡
በሌላ በኩል ለለውጥ ሠራዊት ግንባታ የተሰጠው ትኩረት አናሳ መሆን እና በተደራጀ መልክ አለመሰራቱ፣ የጥናትና ምርምር ስራዎች መጓተት፣ የበጀት አፈጻጸምን በየሩብ ዓመቱ አለመገምገም፣ የሰራተኛውን የውስጥ እርካታ አለመለካት፣የሰራተኛውን አቅም ለመገንባት ጥረት አለመደረጉ እንዲሁም የህዝብ ክንፍ ውይይትን አለማጠናከር በእጥረት ከተብራሩ ጉዳዮች ውሰጥ እንደሚጠቀሱ አቶ ጌታቸው ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም ውይይቱን የመሩት የአካዳሚው ዋና ዳይሬከተር አቶ ከሐሰ ወልደማርያም በማጠቃለያ ንግግራቸው እንደተናገሩት የለውጥ ስራዎችን በማጠናከርና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት እንዲሁም የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባርን በመታገል ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የተገልጋዩን እርካታ ለማሣደግ ጠንክረን መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ አሳስበዋል፡፡ ከህዝብ ክንፍ አካላት ጋር ቋሚ የግንኙነት ስርአት እንዲፈጠርና አደረጃጀቶቹ የራሳቸውን እቅድ አዘጋጅተው ወደ ተግባር እንዲገቡ በማድረግ በተቀመጠው የግንኙነት መርሀ ግብር መሰረት በጋራ በተቀመጡት እቅዶች ዙርያ ግምገማ በማካሄድ የተገልጋዮችን ተጠቃሚነት የሚጎለብትበት አሰራር ከመፍጠር አኳያ ውስንነት ያለ በመሆኑ በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራበት ይገባል ብለዋል ፡፡
እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለፃ አካዳሚው በራሱ ግቢ ትምህርትና ስልጠና ለመስጠት ማነቆ የሆነበትን ጉዳይ ለመፍታት አያት አካባቢ ጊዜያዊ ህንፃ ግንባታ በመገባደድ ላይ ሲሆን እንዲሁም ጎሮ አካባቢ ደግሞ ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ግዙፍ የሆነ የትምህርትና ስልጠና ማዕከል ለመገንባት በቅድመ ዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
በውይይቱ ላይ ከአዲስ አበባከተማ የውጣጡ የሴትና የወጣት ሊግ፣ የወጣት እና ሴት ማህበራት ተወካዮች በውይይቱ የተሣተፉ ሲሆን የተለያዩ ጥያቄዎችን አንሰተው የሚመለከታቸው አካላት ምላሽ ሰጥተውበታል፡፡ በመጨረሻም በ2010 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኋላ እንዲፀድቅ ተደርጓል፡፡

Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published.