የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ አመራርና ሰራተኞች ታላቁን የህዳሴ ግድብ ጎበኙ

stfየአካዳሚው አመራርና ሰራተኞች ሚያዝያ 19 ቀን 2009 ዓ.ም ታላቁን የህዳሴ ግድብ በጎበኙበት ወቅት እንደተናገሩት ይህ ወደር የማይገኝለትና ብሄራዊ መግባባት የተፈጠረበትን ታላቅ ፕሮጀክት ከቦታው ድረስ ተገኝተን በአካል በመጎብኘታችን ታላቅ ደስታ ተሰምቶናል ብለዋል፡፡
ልዩነቶቻችን እንደተጠበቁ ሆነው በሚያግባቡን ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ የማንሰራው ስራ እንደሌለም ዳግም ያስመሰከርንበት ግድብ መሆኑን መረዳት ችለናል ያሉት ጎብኝዎቹ አሁንም ይህን ሀያልና አለምን ጉድ ያሰኘውን መተባበር አጠናክረን በመቀጠል የተገባደደውን ስራ በአጭር ጊዜ ውስጥ ዳር እንደሚያደርሱት ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡
የአካዳሚው አመራና ሰራተኞች አያይዘውም ግድቡ ከተጀመረ አንስቶ እስካሁን ድረስ የምንችለውን ያህል ከወር ደመወዛችን ድጋፍ ስናደርግ ቆይተናል፤በቀጣይም ስራው እስኪጠናቀቅ ድረስ ድጋፋችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ቃል ገብተዋል፡፡
የአካዳሚው ዋና ዳይሬክተር አቶ ካህሰ ወልደማርያም በበኩላቸው እንደገለፁት ኮርፖሬሽኑ በገባው ቃል መሰረት ግንባታውን በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ እንደሚያስረክብ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም ግንባታው ሲጠናቀቅ ከዚህ በፊት የነበረብንን የስልጠና ቦታ ችግር በመቅረፍ በአዲስ አበባ ከተማ ብቁ አመራር እና የሰው ሀይል ለመገንባት የምናደርገውን ጥረት በማፋጠን ረገድ የጎላ ሚና ይጫወታል ብለዋል

Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published.