የአካዳሚው የልዑካን ቡድን በቻይና የስራ ጉብኝት ማድረጉ ተገለጸ

1-39ከአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ከተለያዩ የስራ ዘርፎች የተወጣጣ የአመራርና የባለሙያዎች የልዑካን ቡድን በቻይና ቤጂንግ ለሶስት ቀናት የስራ ጉብኝት አድርጎ መመለሱን የአካዳሚው ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የአካዳሚክ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሐርጋሞ ሐማሞ ገለፁ፡፡

የልዑካን ቡድኑ በቤጂንግ ቆይታው የቤጂንግ አድምንስትሬሽን ኢንስቲዩትን፤ የቤጂንግ ፕላኒንግ ኤግዚቪሽን አዳራሽን አና የቻይኒስ ገቨርናንስ አካዳሚን በመጎብኘት የልምድ ልውውጥ ማድረጉን የገለጹት ኃላፊው ከጉብኝቱ አንድ የአመራር አካዳሚ ብቁ ትምህርትና  ስልጠና ለመስጠት ማሟላት ያለበትን የሰው ኃይልና ግብአትን፣ የፕሮግራምና የካሪኩለም ቀረፃን፣ የምልመላና ቅበላ ጥራትን፣ የትምህርት አሰጣጥና ምዘና ስርዓትን እንዲሁም የስልጠና ፋይዳ ጥናት ዘዴን  በተመለከተ ትምህርት የተወሰደ መሆኑን አያይዘው ተናግረዋል፡፡

ከልዑካን ቡድኑ አባላት ውስጥ አንዱ የሆኑት የብቃትና ውጤታማነት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት  ዳይሬክተር አቶ ውብታየ ባቲ ከጉብኝቱ የተገኘው ልምድ ወደፊት አካዳሚውን ለማጠናከር እድል የሚሰጥ መሆኑን በመግለጽ በተለይ የቤጂንግ አድምንስትሬሽን ኢንስቲዩት ብቁ መምህራንን አሟልቶ  በየደረጃው የሚገኙ አመራርና ባለሙያዎችን እሰከ ማስተርስ ዲግሪ በማሰልጠን ለከተማውና ለጠቅላላ ሀገሪቱ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከት መቻሉን አካዳሚያችን በተሞክሮነት ሊወሰደው የሚገባ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

 

Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published.