የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና አመራሮች በአዲስ አበባ የሚገኙ ፖሊቴክኒክ ኮሌጆችን ጎበኙ

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ስራ በአግባ ተግባራዊ እንዲሆን ከተፈለገ መጀመሪያ አመራሩ ለተልዕኮ ብቁ መሆን አለበት፡፡ ይህንንም በመገንዘብ የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት ከአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ጋር በመተባበር ከመስከረም ስምንት እስከ መስከረም ሠላሣ 2011 ዓመተ ምህረት ድረስ ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ለተወጣጡ ከ600 በላይ አመራሮች ስልጠና ሲሰጥ ቆይቷል፡፡
news4አመራሮች ከንድፈ ሀሳብ ስልጠና ባሻገር መሬት ላይ ያለው ተጨባጭ ተግባር ምን
እንደሚመስል እና ተሞክሮ መቅሰም እንዲያስችላቸው በማሰብ ሁለቱ ተቋማት በጋራ በመተባበር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኙ የነፋስ ስልክ፣ ተግባረዕድ እና የጄኔራል ዊንጌት ፖሊቴክኒክ ኮሌጆችን ጎብኝተዋል፡፡
ከጉብኝቱ ተሳታፊዎች መካከል አቶ አረጋኸኝ ይመር እና ወይዘሮ ንግስት መላኩ በሰጡት አስተያየት ስልጠናው
news1በዘርፉ የተሰጡ ተልዕኮዎችና ግቦችን ለመፈፀም የሚያስችል አቅምና ብቃት ፈጥሮልናል ብለዋል፡፡ በወሰድነው ስልጠና መሰረት ከሌሎች ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ጋር በመጣመር የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ለሀገሪቱ ቁልፍ ሚና እንዳለው ሰልጣኙ በውል እንዲገነዘብ ዕድል ፈጥሮለታል፡፡ ከስልጠናው ባሻገር ትምህርታዊ ጉብኝት ማድረጋችን ደግሞ የበለጠ ስልጠናውን በተግባር ያየንበትና ተሞክሮ የወሰድንበት ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡
እንደ አስተያየት ሰጪዎቹ ገለፃ ለጉብኝት የተመረጡት ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች በቂ ልምድ ያላቸውና የተደራጁ መሆናቸው የምንፈልገውን ልምድ እንድንወስድ ረድቶናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ እንዲህ ዓይነት ጉብኝቶች ስልጠናን በመጠበቅ ብቻ ሳይሆን መደረግ ያለባቸው በየትኛውም ጊዜ ፕሮግራም ተይዞላቸው ቢካሄዱ በዘርፉ ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም በጉብኝቱ ያገኟቸውን ተሞክሮዎች በመውሰድ እንደሚያሰፏቸው ያብራሩት ሰልጣኞቹ ጉብኝቱን ያዘጋጀው አካል ምስጋና ይገባዋል ሲሉም ጨምረው ገልፀዋል፡፡

Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published.