የተያዘውን የጋራ ግብ ለማሳካት ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ

hargamoበሀገራችን ብሎም በከተማችን የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ ለማስቀጠል መንግስት የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ ይህንንም ተከትሎ ከተማ አስተዳደሩ የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር ሆነው እንዲያገለግሉ አቶ ሀርጋሞ ሀማሞን ሾሟል፡፡ የአካዳሚው አመራርና ሰራተኞችም ነሀሴ 22 ቀን 2010 ዓመተ ምህረት ለአዲሱ ዋና ዳይሬክተር አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
በአቀባበል ስነ-ስርዓቱ ላይ አዲሱ የአካዳሚው ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀርጋሞ ሀማሞ እንደተናገሩት ቀደም ብሎ አካዳሚውን በመመስረት፣ በእግሩ እንዲቆም የአሰራር ስርዓት በመዘርጋትናሰራተኞችእንዲመዋሉ በማድረግ ረገድ የበኩላቸውን አሻራ የተወጡ ቢሆንም ከተማ አስተዳደሩ በሰጣቸው ተልዕኮ ተቋሙን መልቀቃቸውን አስረድተዋል፡፡
ከለውጡ ጋር ተያይዞ በድጋሚ ከተማ አስተዳደሩ ተመልሼ ተቋሙን እንዳገለግል ሲመድበኝ ከምንም በላይ ደግሞ ግማሹን የዕድሜ ዘመኔን ትምህርት ላይ ያሳለፍኩ በመሆኔ ወደ እዚህ የትምህርትና የስልጠና ተቋም ስመጣ ደስታ ተሰምቶኛል ሲሉ አብራርተዋል፡፡ አዲሱ ዋና ዳይሬክተር ተቋሙን ስቀላቀል የኔ ሚና የሚሆነውማስተባበር ሲሆን በተቀመጠው አደረጃጀት መሠረት ስራዎችን ትኩረት ሰጥቶ መስራት ደግሞ ከተቋሙ ማህበረሰብ የሚጠበቅ ሀላፊነት ይሆናል፡፡ አደረጃጀቶች ይኑሩ እንጂ የጋራ የሚያደርገን አንድ ግብ አለ፡፡ ይኸውም የአመራርን አቅም መገንባት ነው፡፡ ይህን የጋራ ግብ ለማሳካት ደግሞ ሁሉም ሰራተኛ እኩል ጠቀሜታ ስላለው የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡ ንቦች የራሳቸው የሆነ የግል ተግባር አላቸው፤ ነገር ግን መጨረሻ ላይ ስራቸው ተደምሮ ጣፋጭ የሆነ የማር እንጀራ ይሠራሉ፡፡ እናንተም እንደንቦቹ የተሰጣችሁን ተግባር በትኩረት በመፈፀም ጣፋጭ የሆነ የጋራ ውጤት ማስመዝገብ ይጠበቅባችኋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ hargamo 1

Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published.