የባህል ምሽቱ ሀገራችን የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦች እናት መሆኗን የተገነዘብንበት ነው ሲሉ የሁለተኛ ዙር የመካከለኛ አመራር ሰልጣኞች ተናገሩ፡፡

የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል አንዱ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችን በልማታዊና ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ የተቃኘ ስልጠና በመስጠት ብቁ አመራር መገንባት ነወ፡፡
በዚህ መሰረት የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ከፌዴራል መለስ አካዳሚ ጋር በመተባበር ከአራቱም ብሔራዊ ድርጅቶችና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ለተወጣጡ ከ500 በላይ የሁለተኛ ዙር መካከለኛ አማራሮች ስልጠና ሰጥቷል፡፡ ሰልጣኞች ከዋና ስልጠናቸው ባሻገር የተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮችን፣ መዝናኛዎችንና የባህል ምሽት በማካሄድ የእርስ በርስ ግንኙነታቸውን እንዲያጠናክሩ ታስቦ እንደሚዘጋጅ የአካዳሚው የግንኙነተና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደርቤ ፈለቀ ተናግረዋል፡፡
እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ ሀገራችን የተለያዩ ቋንቋዎች፣ ባህሎች፣ ታሪክ፣ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ያላት ሀገር ናት፡፡ አመራሮችም ከስልጠና ጎን ለጎን የሀገሪቱን ባህልና ወግ ማንፀባረቅ አለባቸው፡፡ በዚህ የባህል ምሽትም ዴሞክራሲያዊ ብሄርተኝነት ጎልቶ የወጣበት ግንኙነታቸውንምያጠናከሩበት ዝግጅት እንደነበረ ጠቁመዋል፡፡

ከባህል ምሽቱ ተሳታፊዎች መካከል ወ/ሮ ብዙአየሁ መኮንን እና አቶ ገብረፃድቃን ፍስሀፅዮን እንደተናገሩት በዚህ የባህል ምሽት ኢትዮጵያን በአንድ አዳራሽ ውስጥ ያየንበት ምሽት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ምንም እንኳ በዚህች አጭር ጊዜ ውስጥ የሀገራችን ባህል፣ ወግ፣ እና ታሪክ ዘርዝረን ማሳየት ቢያስቸግርም ሁሉም ሰልጣኝ የአካባቢውን ባህል ለማስተዋወቅ ያደረገው ጥረት ግን የሚያበረታታ ነው ያሉት ሠልጣኞች እንደዚህ አይነት ፕሮግራሞች ባህልን ከማስተዋወቅ ባሻገር አብሮነታችንን በማጠናከር ረገድ ፋይዳቸው ከፍተኛ ስለሆነ ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል፡፡

Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published.