የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

6የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋጋጥ የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር የአካዳሚ ስርዓተ ጾታ ክፍል  እየሰራ እንደሆን ተገለጸ ፡፡

የአካዳሚው የስርዓተ ጾታ ክፍል  የሴቶችን ተሳትፎ ለማጠናከርና አቅማቸውን ለመገንባት የአካዳሚውን ሴት ሰራተኞች   በተለያዩ ስልጠናዎች እያሳተፈ እንደሆነ የስርዓተ ጾታ ክፍል ኃላፊ የሆኑት ወ/ሪት አዜብ ገበያ ተናግረዋል ፡፡

የሴት ሰራተኞችን አቅም ለማሳደግ በመሰረታዊ የኮምፒውተር አገልግሎት አጠቃቀም ፤ በኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከል ዙሪያ ና  በመረጃ አያያዝ  ላይ ተከታታይነት ያለው ስልጠና እየተሰጠ  እንደሆንና በአዲስ አበባ ከተማ በክፍለ ከተሞችና በወረዳ የሚገኙ ሴት አመራሮችን የአመራር ብቃት ለማሳደግ መረጃ የማሰባሰብ ስራ እየተሰራ መሆኑን ኃላፊዋ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published.