የልምድ ልውውጡ የአካዳሚውን ተልዕኮ ለማሳካት ተጨማሪ አቅም እንደፈጠረ ተገለፀ

l1 l2 l3 l4ከአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ከተለያዩ የስራ ክፍሎች የተውጣጡ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በባህር ዳር በወሎና በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም በአማራና በትግራይ አመራር አካዳሚ በታህሳስ ወር 2010 ዓመተ ምህረት መጀመሪያ ላይ የተደረገው የልምድ ልውውጥ የአካዳሚውን ተልዕኮ ለማሳካት ተጨማሪ አቅም እንደፈጠረ የአካዳሚውን ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር ገብረ ምሩፅ ገለፁ፡፡
እንደ ዶ/ር ገብረ ገለፃ አካዳሚው በትምህርትና በስልጠና፣ በምርምርና የማማከር አገልግሎት ላይ አተኰሮ የሚሰራ በመሆኑ ጉብኝት በተካሄደባቸው ዩኒቨርስቲዎችና የአመራር አካዳሚዎቻቸው ከካሪኩለም ቀረጻ፣ ከምርምር ስራዎች አፈጻጸም፣ ጥራትና አግባብነትን ከማረጋገጥ፣ ከኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ማስፈዳፋት ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ከተቋሞቹ የካበተ ልምድ በርካታ ትምህርት ተወስዷል፡፡ የተወሰዱትን ልምዶች ከአካዳሚው የአሰራር መርህና ፖሊሲዎች ጋር በማጣጣም ወደ ትግበራ እንደሚገባ አክለው ገልፀዋል፡
የጉብኝቱ ተሣታፊ ከነበሩበት ባለሙያዎች ውስጥ አንዳንዶች ከጉብኝቱ በቀጣይ አቅም የሚሆን በርካታ ልምዶች መገኘታቸውን በተለይ ከካሪኩለም ቀረፃ፣ ከስልጠና የትኩረት መስክ ልየታና የስልጠና አሰጣጥዘዴ እንዲሁም የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ለትምህርትና ለስልጠና ስራው ያለውን ወሳኝ ድርሻ በተመለከተ ትምህርት ወስደንበታል ብለዋል፡፡
ጉብኝቱ በሁለት ቡድን ተከፋፍሎ የተካሄደ ሲሆን ከአካዳሚክ ጉዳዮች እና ከጥናትና ምርምር የስልጠናና ማማከር ዘርፍ በድምሩ 22 አመራሮችና ባለሙያዎች የተካፈሉ መሆኑ ታውቋል፡፡

Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published.