የለውጥ ኃይሉ እንደ ሰራዊት ተደራጅቶ ለላቀ አፈጻጸምና ውጤት መትጋት አለበት ተባለ

y2 y3 y4 y5 y1dr. gebreየአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊከ ሰርቪስ ቢሮ ጋር በመተባበር ከቢሮ እስከ ወረዳ ለሚገኙ የፐብሊከ ሰርቪስ ጽ/ቤት ኃላፊዎችና ለሪፎርም ስራ ሂደት መሪዎች የለውጥ ሰራዊት ግንባታና ትግበራ በሚል ርዕሰ ከታህሳስ 13-15/2010 ዓመተ ምህረት በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪሰ ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ
በተሰጠው ስልጠና የለውጥ ኃይሉ እንደ ሰራዊት ተደራጅቶ ለላቀ አፈጻጸምና ውጤት መንቀሳቀስ አለበት መባሉን የስልጠናዉ አስተባበሪና የስልጠናና የማማከር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዮሴፍ አርጋው ገለፁ፡፡
በስልጠናው ፐብሊከ ሰርቪሱን የማዘመን ጽንሰ ሀሳብ፣ አስፈላጊነት፣ የሰራዊት ምንነት፣ ሰራዊቱ የሚመራባቸው መርሆዎችና ሊላበሳቸው የሚገቡ ልዩ ባህሪያት እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ አመራር አቅም ግንባታና የልማት ሰራዊት ላይ ያተኮረ የጥናትና ምርምር ስራ በአካዳሚው የአካዳሚክ ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ በዶ/ር ገብረ ምሩጽ ቀርቦ በቡድንና በጋራ ውይይት እንዲካሄድበት በማድረግ የስልጠናዎችን ግንዛቤ የማስፋፋት ስራ መሰራቱን የዘርፍ ኃላፊው ጨምረው ገልፀዋል፡
በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊከ ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ይሰሐቅ ግርማይ የለውጥ ሰራዊት ግንባታ ሂደትና ትግበራ የስትራቴጂክና የታክቲክ ባህሪ እንዳለውና ሰራዊት የመገንባት ዓላማውየኪራይ ሰብሳቢነትን ፖለቲካዊ ኢኮኖሚን በመናድ በምትኩ የልማታዊ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ የአስተሳሰብ ልእልና አግኝቶ እንዲገነባ ማድረግ መሆኑን በማውሳት የፐብሊከ ሰርቪስ ሰራዊት አሁን ያለውን ድህነት ለመቀየር አንድ ሆኖ እንደ ብዙ በመስራት የሀገራችንን ህዳሴ ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት መሰለፍ አለበትማለታቸውን ኃላፊው አስረድተዋል፡፡
በተጨማሪም የሰራዊት ግንባታ ሰራችንና የሪፎርም ስራው የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፆታዎችና ተቀናጅተው የሚፈጸሙ በመሆኑ አጣምረን ልንተገብራቸው ይገባል መባሉን አቶ ዮሴፍ አርጋው አስረድተዋል፡፡
በስልጠናው ላይ ከአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ከፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ከክፍለ ከተሞችና ከወረዳዎች ፐብሊከ ሰርቪስ ጽ/ቤት ሓላፊዎች ስራ ሂደት መሪዎችን የሪፎርም አስተባባሪዎች በድምሩ ከ300 በላይ ሰለጣኞች የተሣተፉ ሲሆን የሰራዊቱን አቅም ለመገንባት በቀጣይ በጋራ ለመስራት በአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመሪር አካዳሚና ፐብሊከ ሰርቪስ ቢሮ መካከል የስምምነት ሰነድ መፈረሙ ተገለጿል፡፡

Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published.