የለውጥ ስራዎችን በአግባቡ በመተግበር የአገልግሎት አሰጣጡን ማዘመን እንደሚቻል ተገለጸ

 
printing-phot155የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ በ2009 በጀት ዓመት የለውጥ ስራዎችን በተጠናከረ መልኩ በማስቀጠል የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዘገብ እንደሚሰራ የአካዳሚው ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የጥናትና ምርምር ዘርፍ ኃላፊ  አቶ ጥላሁን ሮባ ለሰራተኞች በተዘጋጀ  የለውጥ ስራዎች  ስልጠና ላይ ተናገሩ ፡፡

በ2008 ዓ.ም የለውጥ ስራዎችን በተቋማችን ለመተግበር እንቅስቃሴ የተደረገ ቢሆንም አካዳሚው አዲስ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የከተማው ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብትልማት ቢሮ ተቋማትን ለመመዘን ባዘጋጀው መስፈርት መሰረት ሳይመዘን መቅረቱን እና በ2009 ዓ.ም አመራሩንና ፈፃሚውን በበቂ ሁኔታ በማሰልጠን በተደራጀ አግባብ ወደ ተግባር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

በስልጠናውም ላይ የለውጥ ሰራዊት ፅንሰ ሀሳብ ፤ የካስኬዲንግና የምዘና ስርዓት፤ የሞዴል አደረጃጀቶችና ፈፃሚዎች መለያ መስፈርት እና ራስን የማብቃት እቅድ በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ለአመራሩና  ለባለሙያዎች  ስልጠና ተስጥቷል ፡፡

በስልጠናው ላይ የተሳተፉ አንዳንድ ባለሙያዎች እንደተናገሩት መንግስት የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል የተሻለ አፈጻጸም ካላቸው ሀገራት የሚያመጣቸው ምርጥ ተሞክሮዎች ውጤታማነትን በተመለከተ ጥናት ቢያደረግባቸውና ተፈጻሚነታቸውን ይበልጥ ለማሻሻል  የባለሙያውን አቅም መገንባት አስፈላጊ  እንደሆነ ፤ በለውጥ ስራዎች ዙሪያ የሚዘጋጁ  ስልጠናዎች የሚሰጣቸው ጊዜ አጭር ስለሆነ ወደፊት ሊሻሻል እንደሚገባው፤ በተቋሙ  በርካታ ልምድና ክህሎት ያላቸው ባለሙያዎች እንዳሉና የባለሙያዎቹን አቅም ለመጠቀም አካዳሚው ትኩረት መስጠት እንዳለበት ተናግረዋል ፡፡

የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የለውጥ ስራዎች አፈፃጸም ክትትል ድጋፍና ምዘና ዋና የስራ ሂደት መሪ የሆኑት አቶ አየሁ አለማየሁ  የተነሳው አስተያት ትክክል እንደሆን በመጥቀስ መንግስት  አገልግሎት አሰጣጡን ያሻሽላሉ ያላቸውን  የለውጥ መሳሪያዎች በጥናትና በምርምር በማስደገፍ   የለውጥ ሰራዎችን በአግባቡ በመተግበር የመልካም አስተዳደር ችግሮች መቀረፍ እንዳለባቸው ተናግረዋል ፡፡

 

 

 

Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published.