ከአምስት መቶ በላይ የሚሆኑ የሁለተኛ ዙር መካከለኛ አመራር ሠልጣኞች ረጲ አካባቢ እየተገነባ ያለውን የደረቅ ቆሻሻ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት ጎበኙ

የፌዴራል እና የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ በጋራ ባዘጋጁት ሁለተኛ ዙር የመካከለኛ አመራር ስልጠና ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ ሰልጣኞችበዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ቆሼ አካባቢ እየተገነባ ያለውን ከደረቅ ቆሻሻ ሀይል ማመንጨትየሚያስችል ፕሮጀክትግንባታን ነሀሴ 21 ቀን 2009 ዓ.ም ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱ ወቅት የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ኢያሱ ሰለሞን እንደገለፁት ከሶስት ዓመት በፊት ግንባታው የተጀመረው ይህ ፕሮጀክት በአፍሪካ የጀመሪያው ሲሆን በዓለም ላይም የመጨረሻ የሚባለውን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሚጠቀም ፕሮጀክት እንደሆነ አብራርተዋል፡፡ ከ120 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚፈጀው ከደረቅ ቆሻሻ የኤሌክትሪክ ሀይል የሚያመነጨው ፕሮጀክት ግንባታ በአሁኑ ሠዓት ከ94 በመቶ በላይ የደረሰ ሲሆን ከ6 ወር በኋለ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ የሙከራ ስራ እንደሚጀምር አስተባባሪው አክለው ተናግረዋል፡፡
እንደ አቶ ኢያሱ ማብራሪያ በአፍሪካ ትልቁና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም እየተገነባ የሚገኘው ይህ ፕሮጀክት በአዲስ አበባ ከተማ ዋነኛ የመልካም አስተዳደር ችግር እየሆነ የመጣውን የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓት ሙሉ በሙሉ ከመቅረፉም በላይ አካባቢን እና አየርን ከመበከል ነፃ መሆኑ በእጅጉ ተመራጭ እንደሚያደርገው ገልፀዋል፡፡ፕሮጀክቱ ሁለትዮሽ ፋይዳ አለው ያሉት የፕሮጀክቱአስተባባሪየመጀመሪያውና ዋነኛው አዲስ አበባ ፅዱ፣ማራኪና ለጤና ምቹ እንድትሆን ያደርጋል በሌላ በኩል ደግሞ 50 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሀይል በማመንጨት ለሀገራችን ህዳሴ እውን መሆን ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡
በ65 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈው ይህ ፕሮጀክት በቀን ከ1 ሺህ 400 ቶን ወይም ከአራት ሚሊዮን ኪሎግራም በላይ ደረቅ ቆሻሻ የመቀበል አቅም ያለው ሲሆን ለሀገራችን የቴክኖሎጂ ሽግግር የሚፈጥር ከመሆኑም በላይ 10 ሺህ ለሚጠጉ ዜጎችም የስራ ዕድል ይፈጥራል ተብሎ እንደሚጠበቅ አቶ ኢያሱ
አስረድተዋል፡፡ ከደረቅ ቆሻሻው የሚለዩ ቁርጥራጭ ብረቶች በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ወጣቶች በግብዓትነት እንዲውል ይደረጋል ተብሏል፡፡ ቆሻሻን አስከ 800 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በሚደርስ ከፍተኛ ሙቀት ማቅለጥ የሚችል መሳሪያ የተገጠመለት በመሆኑ ማንኛውንም ደረቅ ቆሻሻ የማቅለጥ አቅም አለው ያሉት አስተባባሪው ቆሻሻው ቀልጦ ወደ ፍል ውሀነት ከተቀየረ በኋላ በሚፈጠረው እንፋሎት የኤሌክትሪክ ሀይል እንዲመነጭ ያደርጋል፡፡ የቆሻሻው ቅሪት ወይም አመድ የሚጣል ሣይሆን ለብሎኬትና ተመሳሳይ አገልግሎት እንደሚውል ተናግረዋል፡፡
አስተባባሪው በመጨረሻም እንደተናገሩት ፕሮጀክቱ በቀን ከፍተኛ የሆነ የቆሻሻ ግብዓት ስለሚፈልግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚፈለገው ልክ ቆሻሻ ማቅረብ አንዳለበት አሳስበዋል፡፡
ከጎብኝዎች መካከል አቶ ሰለሞን ዳኜ እና ወ/ሮ ሠናይት ደስታ በሰጡት አስተያዬት ይህን ትልቅ ፕሮጀክት በማየታችው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ገልፀው አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን የአፍሪካም መዲና በመሆኗ ይህ ፕሮጀክትመቋቋሙ ከተማችን ፅዱና ማራኪ እንድትሆን ከማደረጉም በላይ በቆሻሻ አወጋገድ ዙሪያ የሚሰማውን የህዝብ ሮሮ በመፍታት ረገድም ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ተናግረዋል፡፡
እንደ ጎብኝዎቹ አስተያየት ከደረቅ ቆሻሻው 50 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሀይል ያለምንም የአየር ብክለት ማመንጨት መቻሉ በቀጣይ ለሀገራችን ዕድገት መሰረት እየጣልን መሆኑንና ለአረንጓዴ ልማት እየተደረገ ያለውን ጥረት ውጤታማ እንደሚያደርገው ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡ በመጨረሻም አካዳሚው ይህን የመሠለ ፕሮጀክት እንድንጎበኝና ትልቅ ትምህርት እንድንቀስም በማድረጉ ምሥጋና ይገባዋል ብለዋል፡፡

Posted in Uncategorized.

10 Comments

  1. Pingback: strict keto diet

  2. Pingback: buy viagra online cheapest

  3. Pingback: online pharmacy viagra

  4. Pingback: womens viagra

  5. Pingback: canadian generic viagra

  6. Pingback: viagra price

  7. Pingback: cialis tadalafil

  8. Pingback: cialis 10 mg

  9. Pingback: cialis 2 mg

Leave a Reply

Your email address will not be published.