ኢንዱስትሪው ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መርኢኮኖሚ ለመሸጋገር ለሚደረገው ጥረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑ ተገለፀ


የብረታብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ከሚያስተዳድራቸው አነዱ የሆነው የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ሀገራችን ከግብርና መር ኢኮናሚ ወደ ኢንዱስትሪ መርኢኮኖሚ ለመሸጋገር ለምታደረገው ጥረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑ ተገለፀ፡፡ ከ42 በመቶ በላይየሚሆኑት ሰራተኞች ደግሞ ሴቶች መሆናቸውን ከተቀሙ መረዳት ተችሏል፡፡        
 በ1976 ዓ.ም የጦር መሣሪያ በማደስ ነው ስራውን የጀመረው የዛሬው ግዙፉ ኢንዱስትሪ የብረታብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፕሬሽን የቢሾፍቱ አውቶሞቲብ ኢንዱስትሪ፡፡ ኢንዱስትሪው በ2002 ዓ.ም የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ እንዲጎበኙት ከተደረገ በኋላ ባገኘው ትኩረትና ባሳየው መነቃቃት አደረጃጀቱንና የሰው ሀይሉን በማሳደግ የጦርመሣሪያ ተሸከርካሪ ብቻ ከማምረት ባሻገር ገበያ ተኮር ተሽከርካሪዎችን ማምረት መጀመሩን ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡የኢንዱስትሪው ተቀዳሚው ዓላማ ሀገሪቱን ከግብርና መር ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለመሸጋገር በሚደረገው ጥረት ትልቅ ግብዓት የሚሆን የቴክኖሎጂ ሽግግር ማዕከል ሆኖ የድርሻውን መወጣት  ነው፡፡በመሆኑም ከሀገሪቱ ከተለያዩ ክፍሎች ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት በመካከለኛ ደረጃ የሰለጠኑ ወጣቶችን ቀጥሮና በአውት ሶርስ በጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ ለተደራጁ ወጣቶች ድጋፍ በማድረግና ስራውን በመስጠት  የእውቀት ሽግግር እያካሄደ ይገኛል ፡፡ሻበል ሲሳይ አክለውም ኢንዱስትሪው የተለያዩ የጦርና የትራንስፓርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሸከርካሪዎችን በማደስ ፤በመገጣጠምና በመምራት በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ የማይናቅ አስዋጽኦ እያበረከተ ነው ሲሉ ተናግረዋል ፡፡

Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published.