አካዳሚው የመጀመሪያውን ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ

asየአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የመጀመሪያውን ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ህዳር 22 ቀን 2010 ዓመተ ምህረት በጌት ፋም ሆቴል የአካዳሚው አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት መካሄዱን የአካዳሚው ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዘግቧል፡፡
የግምገማ ሪፖርቱን ያቀረቡት የአካዳሚው ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የአስተዳደር ልማት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አሰፋ አስፈራው እንደገለፁት የ2010 በጀት ዓመት ዕቅድ ከመዘጋጀቱ በፊት በ2009 በጀት ዓመት የነበረውን የስራ አፈጻጸም መነሻ በማድረግ የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጐኖችን በማኔጅመንት፣ ከባለድርሻ አካላትና ከህዝብ ክንፍ ጋር በመገምገም ከዚሁ በመነሣት የ2010 በጀት ዓመት ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መገባቱን ጠቁመዋል፡፡ ከአደረጃጀትና አሰራር ተግባር አኳያ ባለፈው በጀት ዓመት ተጀምሮ የተጠናቀቀው የቢፒአር ጥናት መሰረት የምደባ ስራው የተጠናቀቀ ሲሆን የጀኢጂ ምደባ ለማካሄድ ለሠራተኛው ግንዛቤመፈጠሩን እና የምደባ ኮሚቴምተቋቁሞ በቅርብ ጊዜ ወደ ስራ እንደሚገባ በሪፖርቱ ተብራርቷል፡፡
የለውጥ ስራዎች አፈጻጸም የልማት ሠራዊት ግንባታን በተመለከተ ባለፈው ዓመት የነበረውን የ1ለ5 እና የለውጥ ቡድን መልሶ በማደራጀት የተጠናከረ እንቅስቃሴ እንዲኖር ለማድረግ መሞከሩን፤የመልካም አስተዳደር እና የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባርን ለመታገል ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መገባቱንና በየአደራጃጀቶች ትኩረት ተሰጥቶ እየተገመገመ እንደሚገኝ ኃላፊውጠቁመዋል፡፡ ሌላው በሩብ ዓመቱ ከአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ጋር በመተባበር የመካከለኛ አመራር ስልጠና በተሳካ መልኩ መካሄዱ ተብራርቷል፡፡ የሀብት አጠቃቀምን ከማሻሻል፣ የአመራር ትምህርት ውጤታማነትን ከማሣደግ እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጥን ከማሻሻል አኳያና የመሣሰሉ ተግባራት ከሞላ ጐደል በጥሩ ሁኔታ መከናወናቸው ተገልጿል፡፡
በመጨረሻም በዚሁ ሩብ ዓመት የመደበኛ በጀት አፈጻጸም ከ41 በመቶ አለመብለጡ እንዲሁም የካፒታል በጀት አፈጻጸም ዝቅተኛ እንደነበር ተገምግሟል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ የአዳዲስ ቢሮዎች ግንባታ መጓተቱም ተብራርቷል፡፡የህዝብ ክንፍ ተሳትፎ ዝቅተኛ መሆን፣ የውስጥ እርካታ ጥናት አለመደረጉ፣ የ1ለ5 ውይይት መቆራረጥና የመሣሰሉት ጉዳዮች በክፍተት የታየበት ጊዜ እንደነበር በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡ ከቤቱ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ከተሰጠ በኋላ ለቀጣይ እነዚህንና መሰል ተግባራትን ተከታትሎ በመስራት የተሻለ አፈጻጸም ማስመዝገብ እንደሚገባ የአካዳሚው ዋና ዳይሬክተር አቶ ከሀሰ ወልደማሪያም አሳስበዋል፡፡

Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published.