አካዳሚው የሁለትዮሽ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ

aየአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ከኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርስቲ እና ከኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አመራር አካዳሚ ጋር በጋራ ለመስራት የሁለትዮሽ የስምምነት ሰነድ መፈራረሙን የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዘግቧል፡፡b
ስምምነቱ ጥቅምት 30/ 2011 ዓመተ ምህረት በዝዋይ እንዲሁም ህዳር 01/2011 ዓመተ ምህረት በአዳማ ከተማ የየተቋማቱ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን በጥናትና ምርምር ስራዎች፣ በትምህርትና ስልጠና ውጤታማነት፣ በሰው ኃብት ልማት አቅም ግንባታና በማህበረሰብ አገልግሎት አተገባበር ላይ ያተኮረ መሆኑ ታውቋል፡፡d
በስምምነቱ ወቅት የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሐርጋሞ ሐማሞ ከዩኒቨርስቲውና ከአመራር አካዳሚው ጋር ተቀናጅቶ ለመስራት ዛሬ የደረስንበት ስምምነት የመጀመሪያችን አይደለም፡፡ ከዚህ በፊት ባደረግናቸው ግንኙነቶች ለስራችን አጋዥ የሆኑ መልካማ ልምዶችን መለዋወጥ ችለናል፡፡ የትናቱ ግንኙነታችን እርሾ ሆኖ በሀገር ግንባታ ስራው የተጣለብንን ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ነገን በጋራ ለመስራት የዛሬው ስምምነት ላይ አድርሶናል ብለዋል፡፡c
ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ትስስራችን መማማር፣ መደጋገፍና አቅም መገነባባት የሚያስችለን ከመሆኑም በላይ ያለንን ውስን ሃብት በጋራ በመጠቀም ሀገራዊ ተልእኳችን ለማሳካት ትልቅ እድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም የስምምነቱን አፈጻጸም በተመለከተ በየተቋማቱ ዝርዝር እቅድ

ተዘጋጅቶና የጋራ ተደርጎ ወደስራ እንዲገባ አቅጣጫ መቀመጡ

Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published.