አካዳሚው በስርዓተ ትምህርት ቀረፃ ዙሪያ አበረታች ስራ መስራቱ ተገለፀ

getachew1የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ አመራርና ሰራተኞች የ2010 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እንዲሁም በ2011 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ ላይ ውይይት አድረገዋል፡፡
የአካዳሚው የዕቅድ በጀት ዝግጅትና ክትትል ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ደሳለኝ ባቀረቡት ሪፖርት እንደገለፁት አካዳሚው በልማታዊ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ የተቃኘ ትምህርትና ስልጠና፣ጥናትና ምርምር አገልግሎት ሰጥቷል ብለዋል፡፡
የአመራር ስልጠና በዕቅዳችን መሠረት መሄድ ባይችልም ከአምስት መቶ በላይ ለሚሆኑ የሁለተኛ ዙር መካከለኛ አመራሮች ለ42 ቀን ስልጠና የተሰጠ ሲሆን ከስምንት መቶ በላይ ለሚሆኑ አመራሮች ደግሞ አጫጭር ስልጠናዎችን መስጠት ተችሏል፡፡

አካዳሚው በቀጣይ ለሚጀምረው የትምህርት መርሃ ግብር የሚሆን ስርዓተ ትምህርት በመቅረፅ ከባለድርሻ አካላት በተለይም ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዮች በተውጣጡ ምሁራን በማስገምገም ውጤታማ ስራ መስራት እንደተቻለ አቶ ጌታቸው በሪፖርታቸው ገልጸዋል፡፡
ከተወያዮች የተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎችም በስራ ሀላፊዎች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ የ2011 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድም ቀረቦ ሠፊ ውይይት እና ማሻሻያዎች ተሰጥተውበታል፡፡ hall2
በመጨረሻም የአካዳሚው ከፍተኛ አመራሮች በ2010 በጀት ዓመት የታዩ ጠንካራ ጎኖችን የበለጠ በማጠናከርና ዕጥረቶችን በመቅረፍ አካዳሚው በ2011 የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖረው ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ሲሉ ማሳሰባቸውን የአካዳሚው የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዘገባ ያመለክታል፡፡

Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published.