አካዳሚው በሥርዓተ ትምህርት ቀረፃ ዙሪያ ስልጠና ሠጠ

Unti11

የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ በሥርዓተ ትምህርት ቀረፃ ዙሪያ ለተመረጡ የአካዳሚው ከፍተኛ ባለሙያዎች ስልጠና ሰጥቷል፡፡ ስልጠናውን ያመቻቸው የአካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሲሆን  ዳይሬክተሩ ዶክተር ገብረ ምሩፅ እንደገለፁት አካዳሚው በቀጣይ ለሚጀምረው የመማር መስተማር ስራ የሚሆን የስርዓተ ትምህርት ቀረፃ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ የስልጠናው ዋና ዓላማም በቀጣይ በሚዘጋጀው የስርዓተ ትምህርት ቀረፃ በቀጥታ ተሳታፊና አጋዥ የሚሆኑ አካላትን አቅም ለማጎልበት ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡

እንደ ዳይሬክተሩ ማብራሪያ ሥርዓተ ትምህርት ከመቀረፁ በፊት የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል፡፡ በመጀመሪያ የፍላጎት የዳሰሳ ጥናት በማድረግና የትንተና ስራ በመስራት አስፈላጊ መረጃዎችን በመያዝ ፕሮግራሞችን መለየት ተችሏል፡፡ በዚህ መሠረት urban leadership & governance፣ urban economics/ እና urban solution & diplomacy/ የተሰኙ ፕሮግራሞች መለየታቸውን ተናግረዋል፡፡ ከተለዩት ሦስት ፕሮግራሞች መካከል በከተማ አመራርና አስተዳደር ላይ ብቻ የመጀመሪያ የስርዓተ ትምህርት ረቂቅ /draft/ መዘጋጀቱን እና የሁለቱ ፕሮግራሞች ዝግጅት እንዳልተጀመረ የገለፁት ዶክተር ገብረ የስርዓተ ትምህርት ዝግጅቱን የበለጠ ለማጠናከር ሲባል ከባህር ዳር  እና መቐለ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የልምድ ልውውጥ በማካሄድ የተሻለ ተሞክሮ መቅሰም መቻሉን አስረድተዋል፡፡

የሦስቱም ፕሮግራሞች የስርዓተ ትምህርት ቀረፃ እስከ ሰኔ ወር 2010 እንደሚጠናቀቅና ሞጁሎች ተዘጋጅተው ሌሎች አስፈላጊ ጉዳዮች ከተሟሉ በሚቀጥለው 2011 የመማር ማስተማር ስራው እንደሚጀመር ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡

ከሰልጣኞች መካከል ወይዘሮ ምህረት ሀይለመስቀል እና አቶ ጀምበሩ ኢርኮ በሰጡት አስተያየት ስልጠናው ወደፊት አካዳሚው የሚከፍታቸው የትምህርት ፕሮግራሞች  ከሀገሪቱ ፖሊሲና ስራቴጂ ጋር ተገናዝበው እንዲሰጡ ስርዓተ ትምህርት እንዴት መቅረፅ እንዳለብን የተገነዘብንበት ስልጠና ነው ብላዋል፡፡ አሰልጣኙ በከፍተኛ የትምህርት ተቋም የሚሰሩ መሆናቸውና በተለይ በስርዓተ ትምህርት ልዩ ችሎታ ያላቸው መሆናቸው በፊት ከነበረን ዕውት በተሻለ  ግንዛቤ እንድንጨብጥ አድርገውናል፡፡ ስለሆነም የወሰድነውን ስልጠና ወደ ተግባር በመቀየር ጥራቱን የጠበቀ ሥርዓተ ትምህርት ለማዘጋጀት የበኩላችንን አስተዋፅኦ ለማበርከት ተዘጋጅተናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ስልጠናው የኮተቤ ሜትሮ ፖሊታን ዩኒቨርሲቲ መምህር በሆኑት በተባባሪ ፕሮፌሰር በቀለ ወርቄ ለአራት ተከታታይ ቀናት ሀያ ለሚሆኑ ከፍተኛ ባለሙያዎች መሰጠቱን ለመረዳት ተችሏል፡፡  

Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published.