አካዳሚውን ውጤታማ ለማድረግ የቢፒአር ጥናት ማካሄድ አስፈላጊ መሆኑ ተገለጸ

1-17በአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የተሻለ ውጤታማ አደረጃጀትና ቀልጣፋ የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት በተለያዩ ዳይሬክቶሬቶች እና የስራ ክፍሎች የቢፒአር ጥናት እየተካሄደ መሆኑን  የአካዳሚው ዋና ዳይሬከርተር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እስክንድር መኩሪያ ተናገሩ ፡፡

በአካዳሚው የቢፒአር ጥናት ማድረግ ያስፈለገበት መሰረታዊ ምክንያት አሰራሩንና አደረጃጀቱን ለማስተካከል እንደሆነ በመግለጽ የአመራሩንና የባለሙያውን የስልጠናና ትምህርት ፍላጎት ለማርካት እንዲሁም በበቂ ሁኔታ ምላሽ ለመስጠትና አገልግሎት አሰጣጡን ስታንዳርዱን በጠበቀ መልኩ ለማከናወን የጎላ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል ፡፡

ጥናቱን የተሻለ ለማድረግ የሌሎች ተቋማትን የጥናት ሰነድ መመልከት እንደተቻለና ተሞክሯቸውን በመውሰድ እየተሰራ እንደሆነ፤በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሰቲ ተሞክሮዎችን በመውሰድ ለአንዳንድ ጥናቶች በመነሻነት ጥቅም ላይ ማዋል እንደተቻለ ተናግረዋል ፡፡ እስካሁን በነበረው የጥናት ሂደት ውስጥ በጊዜ እጥረት ምክንያት ልምድ እንዲቀሰምባቸው የተለዩ ተቋማት ተሞክሮን በአካል ተገኝቶ መውሰድ ላይ ክፍተት ቢኖርም ችግሮቹን ለመቀነስ ሙሉ ጊዜን በመስጠትና የሌሎችን ተቋማት የBPR ጥናቶችን ከድረ ገፅ በመውሰድና በመዳሰስ የተሻለ ስራዎችን መስራት እንደተቻለ አያይዘው አስረድተዋል ፡፡

አካዳሚውን የተሻለና ውጤታማ ለማድረግ በአካዳሚ እና በጥናትና ምርምር ዘርፍ የሚገኙ የከተማ አመራር ስልጠና ዳይሬክቶሬት፤የስራ አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ፤የአመራር ትምህርት ፕሮግራሞች ዳይሮክቶሬት ፤ የጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ፤ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጅ ዳይሬክቶሬት፤የጥናትና አግባብነት ማረጋጋጫ ዳይሬክቶሬት እና የተማሪዎችና ሠልጣኞች አገልግሎት አንድ ደጋፊ  ዳይሬክቶሬት በጥቅሉ በስድስት አላማ ፈጻሚ ዳይሮክቶሬቶች፤   እና በአንድ ደጋፊ  ዳይሬክቶሬት ፤የ BPR ጥናቶቹ  ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸው ከዳበሩ በኋላ  ለአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀይል ልማት ቢሮ መላካቸውን ገልጸዋል ፡፡

ጥናቱ ተጠናቆ ወደ ተግባር ሲቀየር በዋናነት የተሻለ፣ ውጤታማና ቀልጣፋ  የአሰራር ስርዓትና አደረጃጀት እንደሚኖር፤  ስራዎችን በወጣላቸው ስታንዳርድ መስረት ለመተግበር እንደሚያስችልና የአካዳሚውን ተልዕኮ ለማሳካት ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር   የዋና ዳይሬከርተር ጽ/ቤት ኃላፊው ተናግረዋል፡

 

Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published.