አስራሁለተኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በአካዳሚው ሰራተኞች ተከብሮ መዋሉ ተገለፀ

gechየዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ አመራርና ሰራተኞች በሕገ መንግስታችን የደመቀ ህብረ ብሔራዊነታችን ለህዳሴያችን በሚል መሪ ቃል ለ12ኛ ጊዜ የሚከበረውን የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በፓናል ውይይት አክብረው መዋላቸውን የአካዳሚው ዋና ዳይሬክተር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ እስክንድር መኩሪያ ገለፁ ፡፡
በዓሉን አስመልክቶ የመወያያ ፅሁፍ ያቀረቡት የአካዳሚው ዋና ዳይሬክተር ጽህፈት ቤት ኃላፊ እንደገለፁት በቀደሙት ሥርዓቶች የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ማንነት የተጣሰበት፣ቋንቋ፣ ባህልና ወግ የታፈነበት በአጠቃላይ በጭቆና አገዛዝ ስር የወደቁበት ጊዜ እንደነበር እንዲሁም በየጊዜው የሚወጡ ህገ መንግስቶችም ለመሪዎች ብቻ የተመቹና ህዝቡን ግንዛቤ ውስጥ ያላስገቡ አካሄዶችን የሚከተሉ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
ህዳር 29 የጸደቀው የኢፌድሪ ሕገ መንግስትየኢትዮጵያን ህዝቦች በአካባቢያቸው ተወያይተውና ተከራክረው ስምምነታቸውን ያረጋገጡበትና በመረጧቸው ወኪሎች አማካኝነት በተቋቋመው ህገ መንግስታዊ ጉባኤ የሀገሪቱ የበላይ ህግ ሆኖ እንዲፀድቅ አድርገዋል ያሉት ኃላፊውከዚህጊዜጀምሮ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ማንነታቸውን፣ቋንቋቸውን፣ወጋቸውን እና ባህላቸውን በነፃነት እየተገበሩ እንደሚገኙ ጨምረው አስረድተዋል፡፡
በቀረበው ፅሁፍ ላይም ከተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ከመድረክ ተገቢ ምላሽ ተሠጥቶባቸዋል፡፡
በመጨረሻም የአካዳሚው የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ደሳለኝ ውይይቱን ሲያጠቃልሉ እንዳሉት አሁን ያለንበት ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ረጅም የሆነ አስከፊና መራራ ትግል ውጤት ነው፡፡ አሁንም ይህን ሥርዓት ለማፍረስ እና ኢትዮጵያን ቀድሞ ወደነበረችበት አዘቅት ውስጥ ለመክተት የሚታትሩ ፀረ-ሰላም ሀይሎችን መታገልና ህገ መንግስቱን ተግቶ መጠበቅ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
በዓሉ በሻማ ማብራት፣በፓናል ውይይት እና በተለያዩ ዝግጅቶች በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል፡፡

Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published.