አመራሩ የታላቁ መሪ አሻራ የሆኑ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን በአግባቡ በመፈፀም የተጣለበትን አደራ ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ

Untitledየአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የሚያሰለጥናቸውየሁለተኛው ዙር የመካከለኛ አመራር ሰልጣኞችታላቁ መሪ አቶ መለስ ዜናዊ መስዋዕት የሆነበትን አምስተኛ ዓመት የድህነትን ሀሳብ ታግሎ ያሸነፈ መሪ በሚል መሪቃል ነሀሴ 12 ቀን 2009 ዓ.ም በተለያዩ ዝግጅቶች አስበው ማምሸታቸው ተገለፀ፡፡
የኢፌዴሪ የሴቶችና ህፃናት ሚኒስቴር ሚንስትር ድኤታ ወ/ሮ ብዙነሽ መሠረት 5ኛ ዓመት ዝክረ መለስ መታሰቢያ ምሽት ላይ እንደተናገሩት በ2004 ዓ.ም የታላቁን መሪንመስዋዕትነት ስንሰማ በሀዘን ድባብ የተዋጥንበት እና ተስፋ የቆረጥንበት ወቅት የነበረ ቢሆንም የበለጠ መላ ህዝቡ ራዕዩን ለማስቀጠል በቁጭትና በወኔ ቃል የገባበት ዓመትም እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
እንደ ወ/ሮ ብዙነሽ ገለፃ ታላቁ መሪያችን በመፈቃቀድ እና በእኩልነት ላይ የተመሰረተች አዲሲቷን ኢትዮጵያ የገነቡ በተለያዩ ታላላቅ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ የአፍሪካውያን አንደበት በመሆን ከፍተኛ ሚና የተጫወቱ መሪ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ ሚንስትር ድኤታዋ ጨምረው እንዳብራሩት አመራሩም የእርሳቸው አሻራ የሆኑትን ፖሊሲዎችንና ስራቴጂዎችን ትኩረት ሰጥቶ በመፈፀም የተጣለበትን ታላቅ አደራ የአላንዳች መዘናጋት ሊወጣ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
በተጨማሪም አቶ ቢኒያም አደራ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርየከንቲባው ህዝብ አደረጃጀት ረዳት አማካሪ በበኩላቸው እንደተናገሩት መለስ ከወጣትነት እድሜው ጀምሮ የታገለ እና ረጅም ዓመት መራመድ የሚያስችሉንን ስትራቴጅና ፖሊሲዎች ነድፎ ጥሎልን ያለፈ መሪ ነው ብለዋል፡፡ መለስ ሞቶም እየታገለ ነው ያሉት አማካሪው በትግል ዘመኑ ይከተላቸው የነበሩት የእርሱ መርሆዎች ብልሽታችንን አሁንም እያስተካከሉንና እያደሱን ነው፡፡ታላቁ መሪ ሆኖ እንዳሳየን ሁሉ እኛም የእርሱን ፈለግ ተከትለን ሆነን መገኘት እና ትክክለኛ የተግባር መሪዎች መሆን ይጠበቅብናል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published.