ተቋማዊ ለውጡን ከሀገራዊና ከከተማዋ ለውጥ ጋር አስተሳስሮ መምራት እንደሚገባ ተጠቆመ

dddd4dd3dd1የአዲስ አበባ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት የ2012 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ10 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ነሀሴ 8
እና 9 2012 ዓመተ ምህረት በነጋ ቦንገር ሆቴል በገመገመበት ወቅት ተቋማዊ ለወጡን ከሀገራዊና ከከተማዋ ለውጥ ጋር
አስተሳስሮ መምራት እንደሚገባ ሪፖርቱን ያቀረቡት የዕቅድና በጀት ዝግጅት ክትትል ዳይሬክቶሬት ተወካይ ዳይሬክተር አቶ ዘላለም
ክበበው ገልፀዋል፡፡
የስልጠና ምርምር አገልግሎቶቻን የፍላጎት ዳሰሳ ጥናትን መሰረት ያደረጉ መሆኑ፣ በኮቪድ-19 ሳይበገሩ መረጃዎችን በማሰባሰብና
የትርፍ ጊዜን ሁሉ ተጠቅሞ በቴክኖሎጂ ታግዞ የጥናትና ምርምር ስራዎች እንዲጠናቀቁ መደረጋቸው በአወንታ የሚጠቀሱ
ተጋብራት እንደነበሩ አክለው ተናግረዋል፡፡
ሀገራዊ ለውጡ በሚፈለገው አስተሳሰብ አቅምና ቁመና ላይ ሆነን አገልግሎት መስጠት አለመቻላችን በዚህም የተነሳ የስልጠና
ሞጁሎች በይዘትም ይሁን በአዘገጃጀት በለውጡ የተቃኙ እንዳይሆኑ ተብሎ በክፍተት ተገምግሟል ፡፡

የኢንስቲትዩቱ የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ደርቤ ፈለቀ የኮቪድ-19 ስራዎችን አስመልክተው ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን ወረርሽኙ
በሀገራችን ከተከሰተ በኋላ በፍጥነት ግብረሀይል በማቋቋም ወደ ስራ መገባቱን ተናግረዋል፡፡ ተቋሙ ከመንግስትና ከጤና ተቋማት
የሚወርዱ መመሪያዎችን በመቀበል ለመተግበር ጥረት አድርጓል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ስራ አመራር ኢስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተርና የጥናትና ምርምር ማማከር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ምንደፍሮ ሀይሌ ለውጡን
አስመልክተው ባቀረቡት ሰነድ እና ማጠቃለያ ላይ እንደተናገሩት የተሟላ አገልግሎት መስጠት ከተፈለገ ለውጡን በቁርጠኝነት
ማረጋገጥ ግዴታ ነው፡፡ እናም በዕቅዳችን መሰረት የተሟላ አገልግሎት በመስጠት ተገልጋዩን ማርካትና የተቋሙን ተልዕኮ ማሳካት
ለነገ የማይባል ተግባር በመሆኑ ሁሉም ኃላፊው በአፅንኦት አስገንዝበዋል፡፡
መረጃው የአዲስ አበባ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት የህዝብ ግንኙነት ቡድን ነው፡፡

Posted in Uncategorized.