በጥናታዊ ፅሁፎች ላይ ምክክር ተደረገ

1

በጥናታዊ ፅሁፎች ላይ ምክክር ተደረገ
የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ የስራ አመራር ኢንሰቲትዩት በ2011 በጀት ዓመት ጥናት ባደረገባቸው 3 ጥናታዊ ፅሁፎች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡
1ኛ. “Practice and Challenges of Land Title Administration Service in Addis Ababa”
2ኛ. “Socio-Economic Status of Relocated Households; Evidence from Nifas Silk and Bole Sub-cities A.A”
3ኛ. “Management and Utilization of Public Parks in Addis Ababa” በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ጥናቶቹ የቀረቡ ሲሆን የመሬት ይዞታ አገልግሎት አሰጣጥን አስመልክቶ በኢንስቲትዩቱ መሪ ተመራማሪ የሆኑት አቶ አፈወርቅ ግዛው ባቀረቡት ጥናታዊ ፅሁፍ የአገልግሎት አሰጣጡ ህጋዊ ማዕቀፍ የሌለው መሆኑ፣ የኪራይ ሰብሳቢነት ችግሮች የሚታዩበት እና እስከ ወረዳ ድረስ አደረጃጀት አለመኖር እና መሰል አንኳር ጉዳዮችን ጠቁመዋል፡፡ 2

በሌላ በኩል የመልሶ ማልማት ተነሺዎች የኢኮኖሚ ሁኔታን በተመለከተ በቂ ካሳ እንደማይከፈላቸውና የመሰረተ ልማት ዝርጋታውም ዝቅተኛ መሆን ከዚህ ባለፈም ለተለያዩ የማህበራዊ ችግሮች ተጋላጭ መሆናቸውን በኢንስቲትዩቱ ተመራማሪ የሆኑት አቶ ባህአብሎም አብይ በጥናቱ ያመላከቱ ሲሆን መንግስት አስፈላጊውን ክትትል ማድረግ እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡3

በኢንስቲትዩቱ የስልጠና ፕሮግራሞች ባለሙያ የሆኑት አቶ እስራኤል እንዳለ በበኩላቸው በከተማችን የሚገኙ የህዝብ መዝናኛ ፓርኮች አያያዝና አጠቃቀምን በተመለከተ ጥናታዊ ፅሁፍ አቅርበዋል፡፡ በአዲስ አበባ ከ19 ያላነሱ የህዝብ መዝናኛ ፓርኮች የሚገኙ ሲሆን ደረጃቸውን የጠበቁ ባይሆኑም 14ቱ አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡ ፓርኮቹ ከታለመላቸው ዓላማ ውጪ መዋል፣ የህግ ማዕቀፍ አለመኖር እና በቂ የሆነ መሰረተ ልማት ያልተሟላላቸው ከመሆናቸውም በላይ ለደህንነት አስጊ መሆናቸውንም ጭምር ጥናት አቅራቢው ጠቁመዋል፡፡4

በመጨረሻም በቀረቡ ጥናታዊ ፅሁፎች ላይ ሰፊ የሆነ ውይይት ከተደረገ እና የማሻሻያ ኃሳቦች ከተሰጡ በኋላ ውይይቱ ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡
5

Posted in Uncategorized.