በተግባራዊ ጥናት /Action research/ ዙሪያ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ

training1በአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አማራር አካዳሚ ለዓላማ አስፈፃሚ ሰራተኞች በተግባራዊ ጥናት /Action research/ ዙሪያ ከህዳር 26 ቀን 2011ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት ሲሠጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቋል፡፡ ስልጠናውን ያዘጋጀው የአካዳሚው የሰው ሃብት ልማት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሞገስ አለማየሁ እንደተናገሩት የሠራተኛውን የስልጠና ፍላጎት ጥናት መነሻ በማድረግ የተዘጋጀው ይህ ስልጠና የአመለካከት፣ የክህሎት እና የዕወቅቀት ክፍተቶችን ይሞላል ተብሎ የተዘጋጀ ስልጠና እንደሆነ ገልፀዋል ፡፡
ስልጠናው በተግባራዊ ጥናት ላይ ትኩረት ማድረጉ በቀጣይ ሰልጣኞች ያገኙትን ዕውቀት በመጠቀም በከተማችን የሚታዩ የማህበራዊ እና የኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በጥናት በመለየት መፍትሄ መስጠት ያስችላቸዋል ተብሎ ይታመናል፡፡ ከዚህ ባሻገር አካዳሚው በጥናትና ምርምር ስራ የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካትም ዕገዛ ይኖረዋል ያሉት አቶ ሞገስ ሰልጠናው ያመጣውን ለውጥ አስመልክቶም የስልጠና ውጤታማነት ጥናት እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡
ስልጠናውን የከፈቱት የአካዳሚው ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የጥናትና ምርምር ዘርፍ ሃላፊ አቶ ገረመው ወርቁ እንደተናገሩት ይህ ስልጠና በጥናትና ምርምር ላይ ትኩረት አድርጎ ለሚሰራው የተቋማችን ባለሙያዎች መሰጠቱ የበለጠ አቅማቸው እንዲጎለብትና ውጤታማ ስራ እንዲሠሩ ከፍተኛ እገዛ እነደሚኖረው ተናግረዋል፡፡ ስለዚህ ሰልጣኞች የህን የተግባር ጥናት /Action research/ ስልጠና በትኩረት በመከታተል የአካዳሚውን ተልዕኮ ለማሳካት ጥረት ማድረግ አለባቸው ያሉት ዳይሬክተሩ ስልጠናውን ያዘጋጀው የአካዳሚው የሠው ሃብት ልማት ዳይሬክቶሬትም ከስልጠናው በኋላ ተግባራዊነቱንና ውጤታማነቱን ማረጋገጥ ይኖርበታል ብለዋል፡፡
ከሰልጣኞች መካከል ወ/ሮ ፀሐይ ሰርሞሎ እና አቶ ንጉስ መንግስቴ እንደተናገሩት ከዚህ በፊትም በጥናትና ምርምር ዙሪያ ስልጠናዎች ተሰጥተዋል፡፡ ይህን ስልጠና ለየት የሚያደርገው ግን የተግባር ስልጠና በመሆኑ በቀጥታ ወደ ተግባር የሚያስገባ መሆኑ ነው ብለዋል፡፡ በአካዳሚው የተጀመሩ እና በቀጣይም ለመስራት የታቀዱ በርካታ የጥናትና ምርምር ስራዎች እንዳሉ የተናገሩት አስተያየት ሰጪዎቹ በዚህ መሰረት በተሟላ ዕውቀትና አቅም ለመፈፀም እድል ፈጥሯል፡፡ አሰልጣኙም በዚህ ዘርፍ የተሻለ ልምድ ያለው በመሆኑ ጥሩ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡ ከምንም በላይ ግን ስልጠናው አሳታፊ እና የዕርስ በዕርስ መማማሪያ መድረክ እንዲኖረው መደረጉ ከሁሉም ሰልጣኞች ልምድ መለዋወጥ በመቻሉ ጥሩ ዕውቀት አግኝተንበታል ብለዋል፡፡
training2
በወሰድነው ስልጠና መሠረት ፈጥነን ወደ ስራ በመግባት ውጤት ለማስመዝገብ ተዘጋጅተናል ሲሉ የገለፁ ሲሆን ስልጠናውን ላዘጋጀው ዳይሬክቶሬትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ስልጠናውን በዘርፉ ልምድ ባላቸው የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ የኒቨርሲቲ መምህር በሆኑት በዶክተር ተረፈ ዘለቀ የተሰጠ ሲሆን 22 የሚሆኑ ሰልጣኞችም ስልጠናውን መውሰዳቸውን መረዳት ተችሏል፡፡

Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published.