በስምንት ወራት ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት ይበቃል የተባለው የአካዳሚው ህንፃ ግንባታ አስካሁን እንዳልተጠናቀቀ ተገለፀ፡፡

ayate1
የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ያለበትን የስልጠና ቦታ ችግር ለመቅረፍ እና ብቁ የከተማ አመራር ለማፍራት ራዕይ ሠንቆ የሚንቀሳቀስ ተቋም ነው፡፡ ይህን ተልዕኮ በተሟላ መልኩ ለመፈፀም በማሰብ በሁለት ሳይቶች ግንባታ እያካሄደ እንደሚገኝ ያታወቃል፡፡ የግንባታ በታዎች በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አያት አካባቢ እና በዚሁ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አይቲ ፓርክ አካባቢ ይገኛሉ፡፡
አያት የሚገኘው እና 272 ሚሊየን ብር በላይ የተበጀተለት ተገጣጣሚ ህንፃ ግንባታ ሚያዚያ መጨረሻ 2009 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን ከ8 ወር የስራ ቀናት በኋላ ተጠናቆ አገልግሎት እንደሚሰጥ ውል የተገባ ቢሆንም እስከ ህዳር 6/2011 ዓ.ም ድረስ የተከናወነው 42 በመቶ ብቻ ነው፡፡ የፕሮጀክቱ መሀንዲስ አቶ አበበ ሎባ እንደተናገሩት የህንፃው ዲዛይን ሳያልቅ ወደ ስራ መገባቱ ለህንፃው መዘግየት መሰረታዊ ምክንያት ሲሆን ሌላው በ2009 ዓ.ም ሚያዚያ ላይ ግንባታው ሲጀመር ቀድሞ ክረምቱ በመግባቱ የተነሳ ለስራ አመቺ ባለመሆኑ ምክንያት ግንባታው ተጓትቷል፡፡ በገባነው ውል መሰረት የማስረከብ ግዴታ ቢኖርብንም ኮንስትራክሽን ቢሮ በወቅቱ ዲዛይኑን አፅድቆ ባለመላኩ ለዚህ ችግር መዳረጋቸውን አስረድተዋል፡፡ እንደተቆጣጣሪ መሀንዲሱ ገለፃ የዲዛይን ችግሩ እስከ ጥር 30/2011 ዓ.ም ድረስ ባለመቀረፉ በስራችን ላይ
ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳድሮብን ቆይቷል፡፡ አሁን ግን ከጥቃቅን ችግሮች በስተቀር ሌላ ችግር ባለመኖሩ ስራው በአግባቡ እየሔደ ይገኛል ብለዋል፡፡
ayate2
አማካሪው፣ደንበኛው እና ኮንትራክተሩ ሣይለያዩ በጋራ መስራት እንዳለባቸው ቢታወቅም ከደንበኛው /client/ በስተቀር ያን ያህል የተቀናጀ ስራ ተሰርቷል ብሎ መናገር አይቻልም፡፡ የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ግን በተለየ መልኩ በየቀኑ በመከታተል እና ችግሮችም ሲያጋጥሙ እንዲፈቱ በማድረግ ለተጫወተው ሚና ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን እስከ ሚያዚያ መጨረሻ 2011 ዓ.ም ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጅት እንደሚውል አቶ አበበ ጨምረው ታግረዋለ፡፡
ayate3

ayate4በሌላ በኩል የአካዳሚው ዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑትና የፕሮጀክቱ ተቆጣጣሪ አቶ እስክንድር መኩሪያ በበኩላቸው እንደገለፁት የኮንስትራክሽን ቢሮ፣ ኮንትራክተሩ እና ከአካዳሚው የተውጣጣ ኮሚቴ ተቋቁሞ ክትትልና ግምገማ እየተደረገ ሲሆን አካዳሚያችን ግን በላቀ መልኩ የሚጠበቅበትን ሃላፊነት ተወጥቷል፡፡ ይህ ብቻም አይደለም ግንባታው ፈጥኖ እንዲጠናቀቅ ካለው ፍላጎት የተነሳ የሌሎችንም ስራ ጭምር ሲያግዝ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡ ይህ ሆኖ ግባታው በእጅጉ ዘግይቷል፡፡ በኮንስትራክሽን ቢሮ እና በኮንትራክተሩ መካከል በዲዛይን መዘግየት ምክንያት እንዲሁም በጊዜ መራዘም ጥያቄ ፈጣን ምላሰሽ አለመስጠትን ተከትሎ የሚነሱ ችግሮች እንዳሉ ቢታወቅም ሌሎች አሳማኝ ያልሆነና ተቀባይነት የሌላቸው ምክንያቶችም እንደሚቀርቡ አስረድተዋል፡፡
እነደ ሃላፊው ማብሪያ ምንም ይሁን ምን ኮንትራክተሩ በገባው ውል መሰረት በወቅቱ አጠናቆ የማስረከብ ግዴታ ቢኖርበትም እስካሁን ግን ማድረግ አልቻለም፡፡
በዚህም የተነሳ አካዳሚው ያላስፈላጊ ወጪ እንዲዳረግ ከማድረጉም በላይ ተልዕኮውን በተሟላ መልኩ እንዳይፈፅም ተግዳሮት እንደሆነበት ገልፀዋል፡፡ አማካሪው ኮንስትራክሽን ቢሮውም ህግና ስርአትን መሰረት ባደረገ መልኩ እርምጃ በመውሰድ ግንባታው ባጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ የድርሻውን ፤ሊወጣ እንደሚገባ አቶ እስክንድር በአፅንኦት አስረድተዋል፡፡
የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ፍቃዱ አለሙ በበኩላቸው የሚገነባው ተገጣጣሚ ህንፃ ለከተማችንም ኖነ ለቴክኖሎጂው አዲስ በመሆኑ ምክንያት የራሱ የሆኑ ውስብስብ ችግሮች እንዳሉበት ተናግረዋል፡፡ ማቴሪያሉ ከፋብሪካ ተመርቶ ስለሚወጣ ጊዜ ይጠይቃል፡፡ ከዚህ ሌላ የማሽን ብልሽት ስለነበረባቸው ለግንባታው መዘግየት ምክንያት ሆኗል ዲዛይኑ በመጀመሪያ ከስራ ዝርዝሩ ጋር ሙሉ በሙሉ ፀድቋል ያሉት መሀንዲሱ ቀርቶ የነበረው የሳይት ወርክ እና የአጥር ስራውን ዲዛይን ልከው ያፀደቁ ቢሆንም የስራ ዝርዝር የሌለው በመሆኑ በዚህ ምክንያት የመዘግየት ሁኔታም ተፈጥሮ እንደነበረ አስረድተዋል፡፡
ayate5እንደ አቶ ፍቃዱ ማብራሪያ ይህ ፕሮጀክት አዲስ እንደመሆኑ ተቋራጩ የራሱ ነው፡፡ ዲዛይን የሚሰራው ማቴሪያልም የሚያቀርበው ራሱ ስለሆነ የእኛ ድርሻ በጣም ትንሽ ነው፡፡ ስለዚህ ሀላፊነት የሚወስደው ራሱ ተቋራጩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ስራው በውሉ መሰረት እየሄደ እንዳልሆነ እና በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ቢሆንም በጊዜው ማጠናቀቅ ባለመቻሉ ምክንያት ለአሰሪው መስሪያ ቤት ውሉ እንዲቋረጥ በጊዜው ጠይቀናል፡፡ ነገር ግን አሰሪ መስሪያ ቤቱ ውሉ ቢቋረጥ የሚፈጠረውን ሌላ ችግር ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት እዲቀጥል አድርጓል ብለዋል፡፡ ይህን መነሻ በማድረግ በሠጠነው አቅጣጫ መሠረት አሁን ግንባታው በማፋጠን ላይ እንደሚገኝ እና የፊታችን ሚያዚያ መጨረሻ ላይ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስተባባሪ መሀንዲሱ ጨምረው አስረድተዋል፡፡

Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published.