አካዳሚው ከፌደራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ለተውጣጡ የተክኒክናሙያ ትምህርትና ስልጠና አመራሮች ከመስከረም 8 ጀምሮ ለተከታታይ 23 ቀናት ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና አጠናቋል፡፡
የስልጠናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ የአካዳሚው ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀርጋሞ ሀማሞ እንደተናገሩት ስልጠናው የተዘጋጀው በቀረቡት ሠነዶች ላይ ግንዛቤ እንደሌላችሁ በማሰብ አይደለም፡፡ ሆኖም ግን በስልጠና ሠነዶች ላይ አንዱ ከሌው ያለው ግንዛቤ እና አረዳድ ብሎም የአመለካከት ደረጃ የተለያየ መሆኑን በመገንዘብ የተዘጋጀ ስልጠና ነው ብለዋል፡፡
እንደ አቶ ሀርጋሞ ገለፃ በዚህ ስልጠና የተወሰነ የተቀራረበ የእውቀትና አመለካከት ደረጃ ላይ እንደደረሳችሁ እምነት አለኝ፡፡ ይህን ለማለት ያስደፈረኝ ባደረግናቸው ተከታታይ ግምገማዎችነ በውይይት ክፍሎች ምልከታ በመነሳት ስልጠናው ግቡን መትቷል ብሎ በድፍረት መናገር ይቻላል ሲሉ አብራርተዋል፡፡
ስልጠናው የለኮሰውን ክብሪት አጋዥ በማድረግ ወደ የተቋማችሁ ስትመለሱ ተግባር ላይ በማዋል ሀገራችን ወደ ኢንዱስትሪ ልማት የምታደርገውን ሩጫ ማገዝ ይጠበቅባችኋል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ስልጠናው ውጤታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ባሳያችሁት ትእግስት የታለመለትን ግብ በማሳካታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡ ስልጠናው እንዲሳካ ለተባበሩ ተቋማትምም ጭምር ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ከሰልጣኞች መካከል አቶ ተስፋዬ ኪሮስ እና አቶ መሐመድኑር ሲራጅ እንደታገሩት ስልጠናው ሃገሪቱ ያስቀመጠቻቸውን ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች እንድንገነዘብ አድርጎናል፡፡ በተለይም በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ስትራቴጂዎች ላይ ያለንን ግንዛቤ እንድናሳድግና በተግባርም ውጤታማ ስራ እንድንሰራ አቅም የፈጠረ ስልጠና መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ስልጠናው የተቀራረበ የዕውቀትና የአመለካከት ደረጃን የፈጠረ እንደነበር ተገለፀ
Posted in Uncategorized.