ሴቶችን ወደ አመራርነት ለማምጣት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ

1የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ሴቶች በአመራርነት ላይ ያላቸው ተሳትፎ እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ በሚሉት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያዳረገውን ጥናት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እንዲካሄድበት ማድረጉ ተገለጸ ፡፡
የአገልግሎት አሰጣጥ ጥናቱ በመንግስታዊ ተቋማት የሙያ ብቃትና ምዘና ማዕከል፣ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ፣ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ እና የፍትህ ቢሮዎች ላይ ትኩረት አድርጓል ፡፡
በጥናቱም የተገኘው ውጤት በተቋማት የሚሰጥ አገልግሎት ከግዜ ቆጣቢነት፣ ከወጪ እና ከቅልጥፍ አኳያ የሚታየው ክፍተት በተገልጋዮች እርካታ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እንደአስከተለ የሚያሳይ ነው ተብሏል፡፡
ሴቶችን ወደ አመራርነት ከማምጣት አንጻር በተጠናው ጥናት ላይ የጥናቱ ድምዳሜ እንደሚያሳየው በሴቶች ዙሪያ ፖሊሲዎች እና ስትራቴጂዎች መውጣታቸው አበረታች ቢሆንም በሚፈለገው ደረጃ ተግባራዊ 2
አለመደረጋቸው ሴቶች እኩል ተሳታፊ እንዳይሆኑ አድርጓቸዋል፡፡
2007፤በ2008 እና በ2009 ዓመተ ምህረት ፣ የወንዶችና የሴት አመራሮች በንፅፅር ስታይ የሴቶች ቁጥር እያነሰ ሲሄድ የወንዶች ቁጥር እየጨመረ መሄዱን ያሳያል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከወረዳ ወደ ክፍለ ከተማ ከክፍለ ከተማ ወደ ከተማ መዋቅር ሲታይ በአመራር ደረጃ ያሉ ሴቶች ቁጥር እየቀነሰ መሄዱ ጥናቱ አመላክቷል፡፡3
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሊግ ሰብሳቢ የሆኑት ወ/ሮ የሺ ወልዴ እንደተናገሩት አካዳሚው ሴቶችንና ሌሎች በከተማው ያሉ ችግሮችን ለመፍታት የውይይቱ ተሳታፊዎች እንደተናገሩት አካዳሚው ያካሄደው ጥናት ጥሩ ቢሆንም ጥናቱ ያሳያቸው ችግሮች እንዲስተካከሉ ተገቢውን ክትትል መደረግ እንዳለበት ገልጸዋል ፡፡

Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published.