በአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ የስራ አመራር ኢንስቲትዩት የኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት በአነስተኛ የስራ መደቦች ላይ ለሚገኙ የተቋማችን ሰራተኞች በመሰረታዊ የኮምፒውተር ክህሎት ዙሪያ ያተኮረ ስልጠና ሰጥቷል፡፡
የስልጠናው ዋና አላማ የኮምፒውተር አጠቃቀም አቅማቸውን ለማሳደግ ያለመ ሲሆን ከዚህ ባሻገር ተቋሙ እየተገበረ ለሚገኘው የተቀናጀ የመረጃ ስርዓት /ERP/ በቀላሉ እንዲጠቀሙ እንደሚረዳቸው በኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ባለሙያ የሆኑት ወይዘሮ ጽዮን ክፍሌ ተናግረዋል፡፡
ስልጠናው ለተከታታይ 10 ቀናት የተሰጠ ሲሆን 25 ሰልጣኞችም ተሳታፊ ሆነዋል፡፡