ለንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማና ከወረዳው ለተውጣጡ ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ

1-23ለንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማና ከወረዳው ለተውጣጡ ባለሙያዎች የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ለ5 ተከታታይ ቀናት በሞጅውል ዝግጅትና በሪፎርም ስራዎች ዙሪያ ለአሰልጣኞች የሰጠው ስልጠና የባለሙያውን አቅም በመገንባት ረገድ ጉልህ   ድርሻ እንዳለውና ሰልጣኞች በነበራቸው ቆይታ ተገቢውን እውቀት ማግኘት እንደቻሉ የስልጠናው ተሳታፊዎች ተናገሩ፡፡

አካዳሚው ከክፍለ ከተማና ከወረዳዎች ጋር ያለውን ግኑኙነት በማጠናከር በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ  አመራሩንና ባለሙያዎችን  በማሰልጠን የመፈጸም አቅምን የማጠናከር ስራ ተከታታይነት ባለው መልኩ መስራት እናዳለበት በመግለጽ የዚህ አይነት ስልጠናም ቀጣይነት  ሊኖረው እንደሚገባ አንዳንድ ሰለልጣኞች   ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የስልጠና ዳይሬክቶሬት የአመራር ስልጠና ፕሮግራሞች  ብድን መሪ የሆኑት ወ/ሮ ምህረት ሀይለ መስቀል  አካዳሚው በዋናነት ባለሙያውንም ሆነ አመራሩን የማብቃት ስራ እንደሚሰራና  ከክፍለ ከታማ እና ከወረዳ የሚላኩ አመራሮችንና ባለሙያዎችን  አቅም በማጎልበት የመፈጸም ብቃታቸውን የማሳደግ ስራ በተከታታይ እየሳራ መሆኑን ገልጸው ከስልጠናው በኃላ ሰልጠኞች የራሳቸውን የግል ጥረት በማከል ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት በመስጠት የህብረተሰቡን እርካታ ማረጋገጥ እንዳለባቸው   ተናግረዋል፡፡ በስልጠናው ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ ለነበራቸው ሰልጣኞችም የምስክርና የምስጋና ወረቀት ተሰጥቷቸዋል፡፡

 

Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published.