ሁሉም የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች ለሠላም ዘብ በመቆም ለውጡን እንዲያስቀጥሉ ጥሪ ቀረበ፡፡

ሁሉም የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች ለሠላም ዘብ በመቆም ለውጡን እንዲያስቀጥሉ ጥሪ ቀረበ፡፡
12የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ የስራ አመራር ኢንስቲትዩት የ2012 በጀት ዓመት የ1ኛውን ሩብ ዓመት ሪፖርት ገምግሟል፡፡ በሪፖርቱ በሩብ ዓመቱ የተከናወኑ ተግባራት ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ በጥንካሬ የታዩ ተግባራትን የበለጠ በማጠናከር ክፍተት የታየባቸውን ደግሞ ፈጥኖ በማስተካከል የተሻለ ስራ መስራት እንደሚገባ ሪፖርቱን ያቀረቡት የዕቅድ በጀት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ደሳለኝ ተናግረዋል፡13

በሌላ በኩል ተቋሙ የያዘውን ዕቅድ በማሳካት ለከተማችን ብሎም ለሀገራችን ዕድገት የበኩላችንን አሻራ ማሳረፍ ይኖርብናል ሲሉ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀረጋሞ ሃማሞ ገልፀዋል፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ ሁላችንም ለሰላም ዘብ በመቆም ለውጡን ማስቀጠል ስንችል ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ በተለይ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ አገር አፍራሽ የሀሰት መልዕክቶችን ከማስፋፋትና ከመከተል በመቆጠብ ኢትዮጵያን ከጥፋት መታደግ የዜግነት ግዴታችን ሊሆን ይገባል ሲሉ በአፅንኦት አስገንዝበዋል፡፡

Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published.